አማራ
ከአማራ ክልል የተገኙት ተረቶች የተሰበሰቡት በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በመጋቢት ወር 1989 ዓ.ም. ሲሆን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ባልደረባ በሆኑት በአቶ አለማየሁ ገብረህይወት የበላይ ተቆጣጣሪነት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ ተራኪዎቹ ከተሰበሰቡ በኋላ ተረቶቹ በዳንኤል ለገሠ የተተረጎሙ ናቸው፡፡ በባህርዳር ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ በህዳር ወር 1991ዓ.ም. በተደረገ ጉብኝት ወቅት ተረቶቹ የብሪትሽ ካውንስል ሰራተኛ በሆነው በመስፍን ሃብተማሪያም ተተርጉመዋል፡፡ ከእነዚህ ተረቶች ውስጥ ተመርጠው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለትምህርት ቤት መማሪያ ይሆኑ ዘንድ በአማራ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ በአቶ ብቅአለ ስዩም አስተባባሪነት በመፅሃፍትነት ታትመዋል፡፡ መለሰ ጌታሁን ወልዴ፣የአማራ ተረት ተራኪ በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ አስገራሚ ከሆኑ ክስተቶች አንዱ አንዳንድ ታሪካዊ ሰዎች (ለምሳሌ፤ አፄ ሃይለስላሌ፣ እቴጌ መነንና ራስ ሀይሉ) በከፊል የመለኮታዊነትን ባህሪ መላበሳቸው ነው፡፡ ብልህና አታላይ የነበሩት የአለቃ ገ/ሃና ገፀ ባህሪ ምናልባትም ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣውና በቋንቋም ሆነ በባህሪ በአፄዎቹ ፍርድ ቤቶችና በጎጃሙ ራስ ሃይሉ ፍርድ ቤትም ጭምር ልቅ ነፃነት የሚታይበት የንጉስ አጫዋቾችታሪክ ነው፡፡ በአማራ ክልል ያሉ ተራኪዎች ብዙዎቹን ተረቶች ማስታወስ ባለመቻላቸው በምትኩ አጫጭር ቀልዶችን፣ አባባሎችንና ግጥሞችን ተናግረዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮቹ ምሉዕ ይሆኑ ዘንድ በስብስቡ ውስጥ ተካተዋል፡፡ ይዘት፤
የድምጽ ቅጂዎች
|