ንጉስ ቴውድሮስና የሞተው ጠባቂ
በወርቁ መርሻ የተተረከ
ንጉስ ቴውድሮስከ 1847-1860 የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አፄ ቴውድሮስ 2ኛ አገራቸው ከምእራቡ አለም ልምድ እንድትቀስም ይጥሩ የነበሩ ዘመናዊ መሪ ነበሩ፡፡ ሆኖም መሣሪያ ከከለከሏቸው እንግሊዞች ጋር ተቃቅረው ስለነበር በርካታ እንግሊዛውያንንና ሌሎች ምእራባውያንን፣ ሚሲዮናውያንን ጨምሮ አግተዋቸው ነበር፡፡ ይህም የእንግሊዛውያንን ወረራ (ከ1859-60) አስከትሎ ታጋቾቹ ተለቀው ቴውድሮስም ራሳቸውን ገደሉ፡፡ የእንግሊዝን ሚሲዮናውያን መፅሐፍ ቅዱስ ሳይሆን ጠመንጃ አምጡልኝ ብለው ይጠይቋቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ንግስት ቪክቶሪያ የጦር መሣሪያ በላኩላቸው ጊዜ መሣሪያውን ለመሞከር ቢፈልጉም ሊቀ ጳጳሱሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪ መጠሪያ ነው፡፡ አቡነ ሰላማ እንዳይሞክሩ ይመክሯቸዋል፡፡
ከጠባቂዎቹ አንዱ ይሞክረው ይሏቸዋል፡፡
እናም አንዱ ጠባቂ መሣሪያውን ሲሞክር ጥይቱ ወደኋላ ተስፈንጥሮ ገደለው፡፡ አፄ ቴውድሮስም ሟቹ ጠባቂ የንጉሱን ፅዋ በመቅመሱ ህዝቡ ሁሉ ያዝን ዘንድ ንጉስ አዘዙ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|