የፕሮጀክቱ ዓላማ
የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በቀላል እንግሊዝኛ መጽሃፍትን በማዘጋጀት በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ተማሪዎች እንግሊዝኛን ማንበብ እንዲለማመዱና እግረ መንገዳቸውንም ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያንጸባርቁትን ተረቶች እንዲያውቁ ማድረግ ነው፡፡
በድምሩ አስራ ሰባት መጽሃፍት የተዘጋጁ ሲሆን እነዚህም በስእላዊ መግለጫዎች ተደግፈዋል፡፡ ለስምንቱ ክልሎች ለእያንዳንዳቸው ሁለት መጽሃፍት እንዲዘጋጁ የታቀደ ሲሆን ለሃረር አንድ መጽሃፍ በእቅዱ ተካቷል፡፡ አዲስ አበባን (ክልል 14) በተመለከተ ለፕሮጀክቱ አመቺነት ሲባል ክልሉ ራሱን የቻለ ክልል ተደርጎ ስላልተወሰደ ምንም የተረቶች ስብስብም ሆነ መጽሃፍ አልታቀደለትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ለድሬደዋም ምንም ስብስብ አልተደረገለትም፡፡ ሁሉም መጽሃፍት ተጽፈው፣ በስዕል ተደግፈውና የገጽታ ዲዛይናቸው የተጠናቀቀ ቢሆንም በገንዘብ ድጋፍ እጥረት ምክንያት ታትመው ለየክልሎቹ የተሰራጩት መጽሃፍት ስምንቱ ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህም በ * ምልክት የተጠቆሙት ናቸው፡፡
የሽፋን ስእሎቹን ያዘጋጁት ዮሴፍ ከበደ (1 እና 2)፣ አጥላባቸው ረዳ (3)፣ ጆን ቾል ጃክ (4)፣ ነጋልኝ ዮሴፍ (5)፣ ለማ ጉያ (6 እና 7)፣ እንዲሁም ታደሰ ወልደአረጋይ (8) ናቸው፡፡
- አፋር
-
- የጫካው ንጉስ*
- መልካሟ ሚስት*
- አማራ
-
- አስማተኛው በትር*
- አላዋቂው ዳኛ
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
-
- ማር አዳኞቹ
- የዝንጀሮው ልጅ
- ጋምቤላ
-
- የጸሃይ መውጣትና ግባት*
- የመጀመሪያው ስጦታ*
- ሃረር
-
- ጻዲቁ ሰውና መንደሪን
- ኦሮሚያ
-
- ቆንጆ ቀያይ ላባዎች*
- የንጉሱ አይጥ ልጅ*
- ሶማሊ
-
- የአንበሳው ሙሽሪት
- የሙሽራዋ ፈተና
- ደቡብ ክልል
-
- የንጉሱ የተፈጥሮ ምልክት
- የባህሯ ልጃገረድ
- ትግራይ
-
- ብልኋ ሴት*
- ወፏና ዝሆኑ
የተመረጡት መጽሃፍት እንደገና በቀላል እንግሊዝኛ በኤልሳቤት ላየርድ የተጻፉ ሲሆን በውስጥ ገጾቻቸው የሚገኙት በጥቁርና ነጭ የተሳሉት ስዕሎች የተሰሩት በዮሴፍ ከበደ ነው፡፡ የመጽሃፍቱ የዲዛይን ሥራ የተከናወነው በእንግሊዝ አገር በሸርሊከር ዉድ ህትመቱ የተከናወነው አዲስ አባባ በሚገኘው በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ነው፡፡
ከተሰበሰቡት ጠቅላላ ተረቶች ውስጥ በመጽሃፍቱ ውስጥ የተካተቱት የተወሰኑት ብቻ ናቸው፡፡ ከመጠን በላይ ብዙ ተረቶች የተሰበሰቡ ሲሆን አንዳንዶቹ በዕድሜ አነስተኛ ለሆኑ ተማሪዎች የሚስማሙ አልነበሩም፡፡ ሆኖም ይህ ስብስብ አስፈላጊ መሆኑ ግልጽ ስለነበረ በእሴትነት መጠበቅ ነበረበት፡፡ ድረ-ገጹም እነዚህን ተረቶች ለሰፊው አንባቢ ያደርሳል ብለን እናምናለን፡፡