ጋምቤላ
በጋምቤላ ክልል ውስጥ ተረቶቹ የተሰበሰቡት በየካቲት ወር1989 ዓ.ም. እና በመስከረም ወር 1990 ዓ.ም. ነው፡፡ ተረቶቹም የተሰበሰቡት የጋምቤላ የትምህርትና ባህል ቢሮ ባልደረባ በሆኑትበአቶ ኦጎታ አጊው ትብብር ነው፡፡ ተረቶቹ ከአኝዋክ በኦጎታ አጊው፣ ከኮሞ በጎሳዬ ተሬሳ እና ከኑዌር በፓስተር ጄምስ ዱዎትዶል ወደ አማርኛ የተመለሱ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ታሪኮች በቀጥታ በአማርኛ የተተረኩ ሲሆን በኦጎታ አጊው እና በብሪትሽ ካውንስሉ ማይክል ዳንኤል አንባቸው ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ የተመለሱ ናቸው፡፡ ቀሲስ ጄምስ ዱዎትዶል፣ የኑዌር ተረት ተራኪ ከጋምቤላ በጋምቤላ ክልል ከሚገኙ አምስት ባህላዊ ስርአቶች የተሰበሰቡት እነዚህ አስደናቂ ታሪኮች ብዙ የእንስሳት ተረቶችን (ለምሳሌ የቀበሮው ታሪክ፣ ጅብ እና ቀበሮ) እንዲሁም በጣም አስገራሚውንና ቅርፁን የሚቀይረውን የሰው በላ ጭራቅን ታሪክ ያካተቱ ናቸው(ንጋፕና ንያክዊ)፡፡ በጣም ተንኮለኛው አቾክና ለዘብተኛው አታላይ አጌንጋ በአኝዋክ ታሪኮች ውስጥ የሚገኙ ገፀ ባህሪያት ናቸው፡፡ ሌቭና ዋሎክ በመዠንገር ታሪኮች ውስጥ እንዲሁም ጋንያ በኑዌር ታሪኮች ውስጥ የሚገኙ የአኝዋኮቹ አቻ ገፀ ባህሪያት ናቸው፡፡ ሰዎችና እንስሳት በሥነ ፍጥረት እንዴት እንደተለዩ የሚለው የአኝዋክ ታሪክ በዘፍጥረት ውስጥ ያለው የያዕቆብ መባረክ አስገራሚ ነፀብራቅ ሲሆን ዓሣን በረጅምና ቀጭን ጦር ማጥመድ የሚለው ታሪክ ደግሞ የነገስታትን ወደ አኝዋክ ህዝቦች መምጣት የሚያሳይ ነው፡፡ ይዘት፤
የድምጽ ቅጂዎች
|