አዱራትና እህቶቿ
በአጁሉ ኦጅዋቶ የተተረከ
አዱራት በጣም በጣም ትንሽ ነበረች፡፡ እህቶቿን ቀጭኔን፣እንቆራሪትንና፣ እባብን ለመምሰል ትሞክር ነበር፡፡ ይህንን ስታደርግ ልጆቿ አይተው እንዲህ አሉ “እናታችን ስትማስን ተመልከቱ፡፡ እናታችን እህቶቿን ለመምሰል ብትሞክርም በጣም ትንሽ ስለሆነች አትችልም፡፡”
ቀጭኔ ልጆቿ “ወጥ ስጭን” ሲሏት “በስሏል” ትላቸዋለች ምክንያቱም ቀጭኔዋ ወጥ ስትፈልግ የራሷን እግር ንክስ አድርጋ የሚወጣውን ዘይት ትጠቀምበታለች፡፡ አዱራት ግን ቀጭኔ ስላልሆነች ይህንን ብታደርግ ስቃይ ይደርስባታል፡፡
እንቁራሪት ልጆቿ “ውሃ ሲጪን” ሲሏት ውሃው እዚያው እንዳለ ትነግራቸዋለች፡፡ ምክንያቱም እንቁራሪት ውሃ አትቀዳም፡፡ እንስራው ላይ ዘላ ወጥታ ሽንቷን ነው የምትሸናው፡፡ እናም አዱራት ይህንን ልታደርግ ብትሞክርም አትችልም፡፡ ብትሞክርም ትሰቃያለች፡፡ በመኝታ ሰዓት ምን ታደርግ ይሆን ብለው ልጆቿ ያስባሉ፡፡
እባቧ በጣም ዘገምተኛ ናት፡፡ ወደ መኝታዋ ስትሄድም ክፍሉን ትሞላውና ልጆቿን ስብስብ አድርጋ ትተኛለች፡፡ አዱራት ግን ልጆቿን ልታቅፍ ብትሞክርም ይህንን ማድረግ የቻለችው እጆቿንና ክንፎቿን በመነቃቀልና እንደ እባቧ ለመርዘም በመሞከር ስለሆነ ሞተች፡፡
ከአቅማችሁ በላይ የሆኑ ሰዎችን ለመምሰል አትሞክሩ፡፡ ራሳችሁን ለመምሰል ሞክሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|