ኦሞ ዞን
በጥር 1993 ዓ.ም. ወደ ጂንካ፣ ቤኔታና ቀይ አፈር በተደረገው ብቸኛ ጉዞ በኦሞ ዞን ካሉት የተለያዩ የጎሳና የቋንቋ ማሕበረሰቦች መካከል ተረቶች ሊሰበሰቡ የቻሉት ከማሊ፣ከአሪ፣ከቤና እና ከጸማይ ህዝቦች ብቻ ነበር፡፡ ጂንካ ውስጥ የተሰራው የፕሮጀክቱ ሥራ እውን ሊሆን የቻለው በክልሉ የባህል ቢሮ ባልደረባ በአቶ ማሞ ማላ እገዛ ሲሆን ሥራውንም በጂንካና በቀይ ዘፈር ያስተባበሩት አቶ ምታቸው በላይ ነበሩ፡፡ የማሊ ተረቶች የተተረጎሙት በይታገሱ ምትኩ ሲሆን የአሪ ተረቶች ደግሞ የተተረጎሙት ዉቸማዮ ዴስሚ ነበር፡፡ የቤናና የጸማይ ተረቶች ግን የተተረኩት በአማርኛ ነበር፡፡ ከአማርኛም ወደ እንግሊዝኛ የተመለሱት በመስፍን ሃብተማሪያም ነው፡፡ የቤና ተረት ተራኪ በጂንካ እንደ ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ተረቶች ሁሉ እነዚህም ታሪኮች ይዘታቸው የሚያጠነጥነው በግብረገብነትና በብልህነት ዙሪያ ነው፡፡ አንዳንዶቹ (እንደ የውሻው ጅራት እና የበሬው ጥጃ) የመሰሉት ታሪኮች በሌሎች ክልሎችም ያሉ ሲሆን ሌሎች ተረቶች ግን ግሩም ወጥነት ያላቸው ናቸው፡፡ዝንጀሮና ጦጣዋ የመጽሐፍ ቅዱስን የባቢሎን ግንብ ታሪክ ያስታውሰናል፡፡ ሁለት ተረቶች ደግሞ የተወሰኑ ጎሳዎችን አመጣጥ ይተርካሉ፡፡ (የቤና አመጣት እና የጸማይ አመጣጥ)፡፡ አንዳንዶቹ ተረቶች ያልተለመዱ ገጸ ባህርያትን (ለምሳሌ፡- ብልጭታና መብረቅ) የያዙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ የጥንት እምነቶችን የሚያንጸባርቁ ምትሃታዊ ፍጡራንንና መንፍሶችን የያዙ ታሪኮችም አሉ፡፡ ይዘት፡:
የድምጽ ቅጂዎች
|