ጠንቋይዋ እና አንዲት ሴት
በእያሱ ኦሪጎ የተተረከ
አንዲት ጠንቋይ ለአንድ ሰው “ከአንድ ወንዝ አጠገብ ስትደርስ በመጀመሪያ የምታገኛትን ሴት ታገባለህ፡፡ ሴትየዋም በቂብ (ቅል) ውሃ ስትቀዳ ታገኛታለህ፡፡ ሰላምታ ሳትሰጣት ቅሉን ብቻ እንድትሰጥህ ጠይቃትና ከቅሉ ትንሽ ውሃ ጠጣ፡፡” አለው፡፡
አንዲት ሴት በመጣች ጊዜ የሚጠጣ ውሃ ጠየቃት፡፡ ውሃውንም ከጠጣ በኋላ ወደቤቷ በመሄድ “ላገባሽ ነው የመጣሁት፡፡” ብሎ ነገራት፡፡
እርሷም ግራ በመጋባት “እንዴት? ለምን?” ብላ ስትጠይቀው “ምክንያቱም ጠንቋዩዋ ነግራኛለች፡፡” አላት፡፡ በዚህም ዓይነት ተጋብተው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|