ወላይታ ዞን
ከወላይታ የተሰበሰቡት ተረቶች በየካቲት 1989 ዓ.ም. አዋሳ ላይ በተረደጉት ማሰባሰቦች ሲሆን ይህም የተሳካው በወቅቱ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ በነበሩት በአቶ አክሊሉ እገዛ ነበር፡፡ ተረቶቹ ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎሙት በብሪቲሽ ካውንስሉ ማይክል አምባቸው ነበር፡፡ ሁሉም ተረቶች የተተረኩት ልዩ የመተረክ ተሰጥኦ ባለው በይስሃቅ አልዳዴ ነበር፡፡ ተረቶቹ ውስጥ ያሉትን ግጥሞች ከማነብነቡም በላይ የተለያዩ ድምጸቶችንም ይፈጥር ነበር፡፡ የእንስሳትን ተረቶች በሚናገርበት ጊዜ የተረቶቹን የማሳቅ ባህሪይ (ለምሳሌ፡- ሰማዩ እየወደቀ ነው) ማንጸባረቅ የቻለ ሲሆን ፍልስፍናዊ ይዘት ያላቸውን (ለምሳሌ፡- ሁሉም ነገር ያልፋል) በጥሩ መልክ አጠቃሎአቸዋል፡፡ ይዘት፡:
የድምጽ ቅጂዎች
|