በቀትር የሚበርዳት አይጠ መጎጥ
በይስሃቅ አልዳዴ የተተረከ
በአንድ ወቅት አንዲት አይጠ መጎጥ ነበረች፡፡ ታዲያ ይህች አይጠ መጎጥ በበጋ ወራት እኩለ ቀን ላይ በጠራራው ፀሃይ ውስጥ ቆማ የበረዳት በመምሰል ትንዘፈዘፍ ነበር፡፡ እናም አንድ ሰው በየቀኑ ይመለከታት ነበርና በየቀኑ በቀትር ከቤቷ ወጥታ በጠራራው ፀሃይ ውስጥ ትንቀጠቀጥ ነበር፡፡
ይኸው ሰው ታዲያ ስለጉዳዩ ማወቅ ፈልጎ ወደ አይጠ መጎጧ በመሄድ “አንቺ አይጠ መጎጥ፡፡” ይላታል፡፡
እርሷም እየተንቀጠቀጠች “ወ,,,,,,,,ወ,,,,,ይ,,,,,,ወ,,,,,,ወ,,,,,ይ ምንድነው የምትፈልገው?” አለችው፡፡
ሰውየውም “ላለፈው አንድ ሳምንት ሙሉ ስመለከትሽ ነበርና በየቀኑ ልክ በቀትር ሰአት ቀኑ እጅጉን በሚሞቅበትና ፀሃይዋም ከአናት ላይ ሆና ሙቀቱ በሚያቃጥልበት ሰአት አንቺ ከቤትሽ ወጥተሽ ልክ ብርድ እንደያዘው ትንቀጠቀጫለሽ፡፡ ይህ ለምንድነው?” ብሎ ጠየቃት፡፡
እርሷም “አይ አንተ ደደብ የሰው ፍጡር! አንተ የምታስበው ስለ አሁን ብቻ ነው፡፡ የወደፊቱን አሻግረህ ስለነገው አታስብም፡፡ በጣም የቅርቡን ብቻ ነውና የምትመለከተው ለምን አሻግረህ ለማየት አትሞክርም?” አለችው፡፡
ሰውየውም በመልሷ ተገርሞ “እባክሽ ለምን እንደምትንቀጠቀጪ ንገሪኝ፣ እባክሽ ንገሪኝ፡፡” አላት፡፡
እርሷም “አይ አንተ ደደብ የሰው ፍጡር፡፡ እንዲያው ምንም አይገባህም አይደል? እኔ እያደረኩ ያለሁት ሰውነቴን በማዘጋጀት ራሴን ከሚቀጥሉት ስድስት ቀዝቃዛ የክረምት ወራት ጋር ከአሁኑ እያላመድኩ ነው፡፡” አለችው፡፡
የዚህም ታሪክ መልእክት አሻግሮ በመመልከት ወደፊት ሊመጣ ለሚችል ችግር ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|