መነሻ ኦሮሚያ
ኦሮሚያ
በዚህ ክልል ውስጥ የተገኙት ታሪኮች ከአዲስ አበባ፣ ጎባ ውስጥ ከሚገኝ አሳሳ ከተባለ አካባቢ እና ሸዋ ውስጥ ከሚገኝ ገብረ ጉራቻ ከሚባሉ ቦታዎች በመስከረም ወር 1990 ዓ.ም. የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ ታሪኮቹን የማሰባሰቡን ስራ ያስተባበረው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ባልደረባ አቶ መርጋ ደበሎ ሲሆን ተረቶቹ ከኦሮምኛ ወደ አማርኛ የተመለሱት በመርጋ ደበሎ እና በበኬር ሃጂ ነው፡፡ ተረቶቹን ወደ እንግሊዝኛ የመመለሱን ስራ የሰራው የብሪትሽ ካውንስሉ ማይክል ዳንኤል አንባቸው ነው፡፡ መርጋ ደበሎና ቦንሳሞ ሚኤሶ በአሳሳ፣ ጎባ በዚህ የበርካታ ተረቶች ስብስብ ውስጥ እንደ የተረገመች እንጀራ እናት፣ አስቸጋሪዋ አማት፣ የአዛውንቱ አባት እውቀት እና የመሳሰሉት አለማቀፋዊ ይዘት ያላቸው አበይት ጉዳዮች ተካተዋል፡፡ አንዳንዶቹ ታሪኮች (ለምሳሌ ተኩላውና ጥንቸሏ) ከጥንት አለማቀፋዊ የታሪክ ውርስ የተገኙ ትረካዎች ናቸው፡፡ ባህላዊ የኦሮሞ ስርአትን በሚያንፀባርቅ መልኩ ብዙዎቹ ታሪኮች የአዛውንቶችን እውቀት መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙትን የፍትህ አሰጣጥ ስርአቶች ባስደናቂ ሁኔታ ይተርካሉ፡፡ ይዘት፤:
የድምጽ ቅጂዎች
|