የአባትየው ምክር
በመሃመድ ኩዩ የተተረከ
በአንድ ወቅት ሁለት ወንድ ልጆች የነበሩት ሰው ነበር፡፡ አንድ ቀን ይህ አባት ልጆቹን ጠርቶ “ልጆቼ ሆይ፣ እኔ መሞቻዬ ደርሷልና ከመሞቴ በፊት የየራሳችሁን ቤት መስርታችሁ ማየት እፈልጋለሁ፡፡
እናም የአንድ ወር ጊዜ እሰጣችሁና ከአንድ ወር በኋላ እዚህ ተመልሳችሁ ላግኛችሁ፡፡” አላቸው፡፡
በዚህም መሠረት ሁለቱም ልጆች ተጣድፈው ከቤት በመውጣት አንደኛው ወደ መንገድ ዳር ሄዶ ዛፎችን በመቁረጥ ትልቅ ቤት መገንባት ጀመረ፡፡
ሁለተኛው ልጅ ግን ወደ ሰዎች በመሄድና ከብዙ ሰዎች በመተዋወቅ ከብዙ ቤተሰቦሰች ጋር የተለየ ግንኙነት መመስረት ጀመረ፡፡(ይህ በኦሮሞ ባህል ከሌሎች ሰዎች ጋር ልክ በደም የመተሳሰር ያህል የወንድምነት ግንኙነት የሚመሠረትበትና በልዩ በአል ላይ አንደኛው የሌላኛውን ሰው ጡት የጠባ በመምሰል ከአንድ ሰው የመወለድን ብሂል በተምሳሌታዊነት የማሳየት ልምድ ነው፡፡) በዚህም መሰረት ሁለተኛው ልጅ ወደ ልዩ ልዩ ሰዎች በመሄድ ለተለያዩ ቤተሰቦች የማደጎ ልጅ መምሰል ቻለ፡፡
ከዚህም በኋላ አንድ ወር በሞላቸው ጊዜ ሁለቱም ወደ አባታቸው ሲመለሱ እሱም “ታዲያ ቤታችሁን ሠራችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ሁለቱም ወንድማማቾች “አዎ” ብለው መለሱለት፡፡
ስለዚህ አባትየው ከመጀመሪያው ልጅ ጋር በመሄድ ልጁ የሰራቸውን ብዙ ጎጆዎች ተመለከተ፡፡ እያንዳንዱ ጎጆ አጠገብ በደረሰም ጊዜ “እዚህ ጎጆ ውስጥ ሰው አለ?” እያለ ይጠይቅ ጀመር፡፡
ልጁም “የለም” ብሎ ይመልሳል፡፡
ከዚያም ወደሚቀጥለው ጎጆ ሲደርስ አሁንም “እዚህ ጎጆ ውስጥ ሰው አለ?” ብሎ ሲጠይቅ ልጁም “የለም” እያለ ይመልሳል፡፡
በኋላ አባትየው የሚያስተናግደው ሰው ስላልነበረና በጣም ስለራበው “ወደ ቤት እንሂድ፡፡” አለ፡፡
ወደ ቤትም ሄደው ሁለተኛውን ልጅ አገኙ፡፡ ሁለተኛውም ልጅ ወደ መጀመሪያው የማደጎ ቤተሰቡ ይዟቸው ሄዶ አባቱን “እነዚህ አባቴና ወንድሞቼ ናቸው፡፡” ብሎ አስተዋወቀው፡፡ ቤተሰቡም በደስታ ተቀብሎ በግ አርዶላቸው ትልቅ ድግስ አዘጋጁላቸው፡፡
ከዚያም ወደ ሁለተኛው የማደጎ ቤተሰብ ወስዶ ሲያስተዋውቃቸው እነርሱም በትልቅ ድግስ በደስታ ተቀበሏቸው፡፡
በዚህ ዓይነት ሁለተኛው ልጅ በማደጎነት ወደተዛመዳቸው ቤተሰቦች ሁሉ በየተራ እየሄዱ ከበሉና ከጠጡ በኋላ አባትየው “የራሳችሁን ቤት ሄዳችሁ ስሩ ያልኳችሁ ይህንን ማለቴ ነበር፡፡ ቤት ማለት የጎጆዎች ብዛት ወይም የትልቅ ቤት ውበት ሳይሆን ከሌሎች ጋር የምንመሰርተው ፍቅር፣ ቅርበትና ወዳጅነት ማለት ነው፡፡” አላቸው፡፡
“አባቴ ሲሞት ሶስት ብልህ አባባሎችን ትቶልኝ ነበር የሞተው፡፡ የመጀመሪያው ሚስቴ ሰርግ ቤት ሄዳ አንዳታድር፤ሁለተኛውም እርጉዝ ፈረሴን ለጓደኞቼ እንዳላውስና ሶስተኛው ደግሞ በቸገረኝ ጊዜ እህቴ ቤት እንዳልሄድ ነበር፡፡ የአባቴንም ምክሮች በሙሉ ፈትሼያቸው በእርግጥም ሁሉም እውነት መሆናቸውን አረጋግጫለሁ፡፡ ይህ የሚስቴ የአንገት ሃብል ነው፡፡ ራሴን ቀይሬ በመሄድ አብሬያት ሰርጉ ቤት አድሬአለሁ፡፡ ታዲያ እውነትም እንግዳ ሰው ሆኜ ብሆን ኖሮ ይህ እምነትን ማጉደል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ፈረሴ ያስጨነገፈችው ጭንጋፍ እግር ሲሆን ጓደኛዬ ክፉኛ ጋልቧት ነበር፡፡ በመጨረሻም ይህ እህቴ የሰጠችኝ እፍኝ ጥሬ ነው፡፡ ስለዚህ የአባቶቻችንንና የአዛውንቶችን ምክር ሁልጊዜ መቀበል አለብን፡፡” አላቸው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|