መነሻ ሶማሊ
ሶማሊ
እነዚህ ተረቶች የተሰበሰቡት በጥቅምት 1991 ዓ.ም. በኦስማን አብዱላሂ አህመድ በመታገዝ ታሪኮቹን ከሶማሊገኛ ወደ አማርኛ በተረጎመውና ጉብኝቱን ባስተባበረው የሶማሌ ትምህርት ቢሮ ባልደረባው በሞጌ አብዲ ኦማር ድጋፍ ነው፡፡ ተረቶቹን ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛየመለሰው የብሪቲሽ ካውንስሉ ሚካኤል ንጉሴ ነው፡፡ አዋላጆች በጂጂጋ ተረት ሲተርቱ ተረቶቹ የአርቢውንና የዘላኑን ሶማሌ ባህላዊ የኑሮ ዘይቤ የሚያንጸብርቁ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ (ለምሳሌ፡- ጭንቅላቱ) በቀይ ባህር ሩቅ ዳርቻዎች ከሚነገሩት ታሪኮች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሲሆን ሌሎቹ (ለምሳሌ፡- ጥቁሩ አሞራ) ከእስላማዊ እምነት መምጣት በፊት የነበሩትን እምነቶች የሚያንጸባርቁ ናቸው፡፡ በጂጂጋ ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ ከሴት ተረት ተናጋሪዎች ጋር መስራት ተችሎ ነበር፡፡ (የደግዴር ተራኪ 12 ዓመት ገደማ የነበረች ሴት ልጅ ናት፡፡) ይዘት፡:
የድምጽ ቅጂዎች
|