ጅብ፣ቀበሮና ጦጣ
በዩሱፍ አደም ማንደሬ የተተረከ
በድሮ ጊዜ ጅብና ቀበሮ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን ተጣልተው ወደ ጦጣ በመሄድ ጦጣዋ ፍርድ እንድትሰጣቸው ጠየቋት፡፡
ጅቡም “ቀበሮው ሌባ ብሎ ሰድቦኛል፡፡” ብሎ ክሱን አቀረበ፡፡ ቀበሮውም ጦጣዋን በስጦታ ሊደልላት ሞከረ፡፡ ጦጣዋም “ክሳችሁን ከማቅረባችሁ በፊት የዋስ ክፍያ የሚከፍልላችሁን መፈለግ አለባችሁ፡፡” አለችው፡፡
ጅቡም “ተያዤ ቀበሮው እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡” ሲል ቀበሮውም ተያዡ ጅቡ እንዲሆን መፈለጉን ተናገረ፡፡ ጦጣዋም በአንክሮ ከተመለከተቻቸው በኋላ “ሁለታችሁም ተሳስታችኋል፡፡ እርስ በርሳችሁ ተያዥ ስለሆናችሁ የእናንተን ጉዳይ የምፈርድበት ምንም ምክንያት የለኝም፡፡ በሁለታችሁ መካከል ጠብ ሳይኖር እንደተጣላችሁ አስመስላችሁ ነውና የመጣችሁት ይህንን ጉዳይ የሚመለከተው ሌላ ዳኛ ቢሆን ኖሮ ለሞኝነታችሁ ብዙ ገንዘብ ይቀጣችሁ ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ የሁለታችሁም የቅርብ ጓደኛ በመሆኔ እያንዳንዳችሁን አምስት አምስት ብርብር በኢትዮጵያ ዋና የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ ብቻ እቀጣችኋለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|