የባለቤትነት መብትና ትርጉም
የባለቤትነት መብትን በተመለከተ
የእነዚህ ተረቶች ህጋዊ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ ማንም ግለሰብ የባለቤትነት መብት የለውም፡፡ ተረቶቹን ማንም ሰው በራሱ ቃላት፣ በራሱ አገላለጽና በማንኛውም መንገድ ማለትም በቃል፣ በጽሁፍ ወይም በኤሌክተሮኒክ ማሰራጫ መልሶ መተረት ይችላል፡፡ ነገር ግን የተራኪዎቹና የተርጓሚዎቹ ቃላት በቀጥታ ተመልሰው በተደጋጋሚ በሌሎች ሰዎች ከተጠቀሱ የተራኪዎቹ ስም (በእያንዳንዱ ተረት አናት ላይ ያለው) መገለጽ አለበት፡፡
የትርጉም ሥራውን በተመለከተ
ጥቂት ቃላት በእንግሊዝኛ ተጓዳኝ ፍቺ ከሌላቸው እንግሊዝኛው ድረ-ገጽ ውስጥ ሳይተረጎሙ እንዳሉ ተቀምጠዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ “እንጀራ” የሚለው ቃል የሚገኝ ሲሆን ይህ ቃል በእንግሊዝኛ ተጓዳኝ ትርጉም የለውም፡፡ እንደነዚህ ያሉት ቃላት በግርጌ ማስታወሻ ውስጥ ወይም በቅንፍ ውስጥ መግለጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡