ቤንሻንጉል ጉሙዝ
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገኙ ተረቶች የተሰበሰቡት በመስከረም ወር 1992ዓ.ም. ነው፡፡ ፕርጀክቱ በአሶሳ ውስጥ ከሺናሻና በርታ ተራኪዎች ጋር የሰራ ሲሆን በቻግኒ ውስጥ ደግሞ ከጉሙዝ ተራኪዎች ጋር ሰርቷል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ የትምህርትና ባህል ቢሮ ባልደረብ የሆኑት አቶ ድረስ ገ/መስቀል ወደ ክልሉ የተደረገውን ጉብኝት እንዲሁም ጉዞንና ተራኪዎቹን በማሰባሰብ ትብብር አድርገዋል፡፡ ተረቶቹ ከሽናሻ ወደ አማርኛ የተመለሱት በሃበሻ ፈይሳ ሲሆን ከበርታ ወደ አማርኛ የተተረጎሙት ደግሞ በካፒቴን ሃሚስ ባላህ እንዲሁም ከጉሙዝ ወደ አማርኛ የተመለሱት በበላይ መኮንን ነው፡፡ ከአማርኛም ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎሙት በመስፍን ሃብተማሪያም ነው፡፡ ኤጋሲ ረታ፣ የጉሙዝ ተረት ተራኪ ከዚህ ክልል የተሰበሰቡት ተረቶች በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ (ለምሳሌ የዝንጀዋ ፍርድ እና ሴቷና አንበሳው) በተለያየ መልኩ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎችም ያጋጠሙ ናቸው፡፡ የአሳ ማስገሩ ታሪክ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሰው የቀይ ባህር ለሁለት መከፈል ታሪክ ጋር የሚያያዝ አንድምታ አለው፡፡ ሌሎቹ ታሪኮች በግልፅ ቱባ ተረቶች ሲሆኑ ባህላዊ እምነቶችንና ስርአቶችን የሚያንፀባርቁ ናቸው (ለምሳሌ፤ አዳኙና ዝሆኑ፣ ማር አዳኞቹና እና የሰው ልጅ አመጣጥ)፡፡ ነገር ግን በዚህ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆነውና ሰፊ ቦታን ባካለለው ክልል ውስጥ ተራኪዎችን ማግኘትም ሆነ ተረት እንዲተርኩ ማበረታታት አስቸጋሪ በመሆኑ የተሟላ ስብስብ ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜን መጠየቁ አልቀረም፡፡ ይዘት፤:
የድምጽ ቅጂዎች
|