መነሻ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዳኙና ዝሆኑ
አዳኙና ዝሆኑ
በበላይ መኩሪያ የተተረከ
በድሮ ጊዜ ወደ ሱዳን በሚወስደው መንገድ ላይ ሰዎች አንድ ዝሆን ያጋጥማቸዋል፡፡ ዝሆንን በአንድ አይነት የጣሊያን ጠመንጃ መግደል ቢቻልም ዝሆኑ ብዙ ውሃ ከጠጣ ግን ጥይቱ አይበሳውም፡፡
ሆኖም ሰዎቹ ይህንን ዝሆን ገድለው ሥጋውን በሙሉ ወደ ቤታቸው ይዘው ሄዱ፡፡ ሥጋውንም ከምረው ካስቀመጡ በኋላ የዝሆኑን ጭንቅላት ግድግዳው ላይ ሰቀሉት፡፡ ታዲያ እነርሱ በሣቁ ጊዜ የዝሆኑም ጭንቅላት ይስቅ ነበር፡፡
“እየሳቃችሁ ነው?” አላቸው የዝሆኑ ጭንቅላት
በዚህን ጊዜ አንድ አዛውንት ሰው ግራ በመጋባት
“ዛሬ ደግሞ ምን አይነት እንስሳ ነው የገደላችሁት ከሞተም በኋላ የሚናገር እንስሳ በጣም ይገርማል” አሉ፡፡
የዝሆኑን ቋንጣም በበሉ ጊዜ ጭንቅላቱ አሁንም ያንኑ ያደርግ ነበር፡፡
አሁንም አዛውንቱ ሰው “ይህ እንዴት ያለ ተዓምር ነው? ሌላ ቦታ ወስዳችሁ ስቀሉት” አሉ፡፡
እርሱም በግጥም
“በደስታ ብታሾፉብኝም
እኔ ግን አልሞትኩም
እኔም የእናንተን ሥጋ እበላለሁ
ገዳዮቼ እናንተ ናችሁ?
ገዳዮቼ እናንተ ናችሁ?
የሞተውስ ማነው?
የሞተውስ ማነው?
በመቀጠልም ጭንቅላቱ
ሥጋዬን እየበላችሁ ነው
እኔም ግን ሥጋችሁን እበላለሁ
አልሞትምም
ከአጥንቶቼ ጋር እኖራለሁ
ሥጋዬ ከእኔ ተለይቶ
እኔ ግን እኖራለሁ” እያለ መዝፈኑን ቀጠለ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|