መነሻ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዝንጀሮና ጦጣ
ዝንጀሮና ጦጣ
በበላይ መኩሪያ የተተረከ
አንድ ዝንጀሮና አንድ ጦጣ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ጦጣውም ብልጥ ስለነበረ በየሰርጉ ላይ ምግብ እየሰረቀና እየጨፈረ ቁዋ፣ቁዋ፣ቁዋ፣ የሚል ድምፅ ሲያወጣ ዝንጀሮም በራሱ መንገድ
ቁዋ፣ቁዋ፣ቁዋ፣ሁም፣ሁም፣ የሚል ድምፅ ያሰማ ነበር፡፡
በእንደዚህም ዓይነት ጓደኛውን እየጠራ ድግሱን አብረው ይመገቡ ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም ይሰዳደቡ ነበር፡፡
“ቁዋ፣ቁዋ፣ አፍንጫ የለህ፣ ቂጠ መላጣ፣ የጋለ ድንጋይ ላይ የምትቀመጥ” እየተባባሉ ቢሰዳደቡም ጓደኛሞች በመሆን እየተጠራሩ ሰብል ከማሣ እየሰረቁ ይበሉ ነበር፡፡ ጦጣውም ዝንጀሮውን “እንዴት እንዲህ ትለኛለህ? እስኪ አሁን እንወዳደርና ማሳው ጋ ቀድሞ የሚደርሰውን እናያለን፡፡”
በዚህ ሁኔታም ይወዳደሩ ነበር አንድ ቀን ታዲያ ጦጣው ዝጀሮውን እስኪ ከዚህ ዛፍ ላይ እንዝለልና ማን እንደሚያሸንፍ እንይ ይለዋል፡፡
ጦጣውም ወደ ውሃ ውስጥ የሚያዘልለውን ሥፍራ መርጦ ውሃው ውስጥ ዘሎ ሲድን ዝንጀሮው ገደል ውስጥ ገብቶ ሞተ፡፡
በዚህም ሁኔታ ብልጡ ጦጣው ብልጥ በመሆኑ ጥሩ ቦታ ለራሱ ሲመርጥ ዝንጀሮው መጥፎ ቦታ መርጦ ለሞት በቃ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|