ምስጋና
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮጀክቱን በበላይ ተቆጣጣሪነት ያስተባበረው ሲሆን ለፕሮጀክቱም ልባዊ ድጋፉን ቸሮታል፡፡ ታሪኮቹን የማስተባበሩ ሥራ የተከናወነው በየክልሉ የባህልና ትምህርት ቢሮ ኦፊሰሮች ሲሆን የእነርሱም ስም በየክልላቸው የተረቶች ስብስብ መግቢያ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሥማቸው ሳይጠቀስ የቀሩ ሰዎች ካሉ ልባዊ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ የስሞች አለመጠቀስና ግድፈቶችን በተመለከተ በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች ፕሮጀክቱ ከአስር ዓመታት በላይ ክፍተት ስለነበረው እነዚህ ችግሮች መከሰታቸው አይቀሬ ነው፡፡
በማይክል ሳርጅንት (ዳይሬክተር ከ1984-1992 ዓ.ም.) አመራር ስር የነበረው በኢትዮጵያ የብሪቲሽ ካውንስል በኤልሳቤት ላየርድ የቀረበውን የመጀመሪያ የፕሮጀክቱ ሃሳብ በደስታ በመቀበል ከፍተኛ ድጋፉን ሰጥቶታል፡፡ በርካታ የካውንስሉ ባልደረቦች በፕሮጀክቱ የተሳተፉ ሲሆን በተለይም ሹፌሮቹ ተክለሃይማኖት ይግለጡና ሟቹ ደረጀ መኮንን በመላው ኢትዮጵያ የተደረጉትን አድካሚ ጉዞዎች በብቃት መወጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ ላይ ከኤልሳቤት ላየርድ ጋር ሶስት ዋና የአማርኛ/እንግሊዝኛ ተርጓሚዎች፤ ማይክል ዳንኤል፣ ሚካኤል ንጉሴና መስፍን ሃብተማሪያም የተሳተፉ ሲሆን ብዙዎቹ ታሪኮች በየክልሉ የባህልና ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎችም የተተረጎሙ ናቸው፡፡ የተርጓዎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታም ከክልል ክልል መጠነኛ ልዩነት የነበረው ቢሆንም ተርጓሚዎቹና አስተባባሪዎቹ ላሳዩት ከፍተኛ የስራ ትጋትና ሙያዊ ድጋፍ ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ለዚህ ድረ-ገጽ አስፈላጊው ግብአት የተዘጋጀው በኤልሳቤት ላየርድና በማይክል ሳርጅንት ነው፡፡ ጋሬት ክሮሚ፣አንተን ኦሊኒክ እና አና ሲድያኪና ድረ-ገጹን በማዋቀሩ ስራ ላይ ሙያዊ የቴክሊክ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ይህ ድረ-ገጽና ተረቶቹ በሙሉ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተተረጎሙት በሽመልስ ለማ ብሩ ሲሆን የአርትዖት ሥራውን የሰራው ዶ/ር ንጉሴ አርዓያ ነው፡፡
ማይክል ዳንኤል አምባቸው |
ሚካኤል ንጉሴ |
መስፍን ሃብተማሪያም |