መነሻ አፋር
አፋር
በዚህኛው ስብስብ ውስጥ ያሉ ተረቶች የተነገሩት በመጋቢት ወር 1989ዓ.ም. በተለያዩ ሁኔታዎች ሲሆን ይኸውም በክልሉ ባህል ቢሮና እንዲሁም በወቅቱ የቢሮው ሃላፊ በሆኑት በአቶ ሙሀመድ አህመድ አልጋኒ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ታሪኮቹ በሙሉ የተራኪዎቹ ባይሆኑም አብዛኛዎቹ በአፋርኛ ቋንቋ ተተርከው በሙሃመድ አልጋኒ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ ናቸው፡፡ አማርኛውም ወደ እንግሊዘኛ የተተረጎመው በብሪትሽ ካውንስሉ ሰራተኛ በማይክል ዳንኤል አምባቸው ነው፡፡ በአሳይታ አካባቢ የሚገኝ የአፋር ቤት አንዳንዶቹ የአፋር ተረቶች በሌላ የኢትዮጲያ ክልሎች ውስጥ ከሚነገሩት ተረቶች ጋር ተመሳሳይነት አላቸው (ለምሳሌ፣ ተንኮለኛው ቀበሮ እና ሶስቱ)፡፡ በአፋር ተረቶች ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የእንቆቅልሽ ብሂል ነው (ለምሳሌ፣ አልጋ ወራሹ ልዑል) ፡፡ይህ በቅርብ ምስራቅ ሀገሮች የሚታየው ጥንታዊ የታሪክ አነጋገር ስልት ነው፡፡ (በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሚገኘውን የሳምሶንን ታሪክ እና የኤዲፐስን አፈ-ታሪክ ማመሳከር ይቻላል፡፡)
ይዘት፤
የድምጽ ቅጂዎች፡-
|