የአዳ–< ሙሽራ
ተራኪው የማይታወቅ
በአንድ ወቅት አንዲት በጣም ቆንጆ የአፋር ልጃገረድ ነበረች፡፡ እናም በፍቅሯ እጅግ የተማረከ አንድ ወጣት ነበር፡፡ ወጣቱም ልጅ ቆንጆዋን ልጅ ለማግባት ሽማግሌዎችን ወደ አባቷ ይልካል፡፡ ነገር ግን አባቷ እንዲህ ሲሉ መለሱ “ልጄን ልሰጠው የምችKው ያለውን ሃብት በሙሉ፣ግመሎቹንና ላሞቹን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ከሰጠኝ ብቻ ነው፡፡”
ሽማግሌዎቹም ይህንን መልስ ይዘው በመመለስ ለልጁ እንዲህ ይሉታል፡፡ “ልጄ ተመልከት፣ የልጅቷ አባት የማይቻለውን ነገር ጠይቀዋል፡፡ ሃብትህንም በሙሉ እንድትሰጣቸው ይፈልጋሉ፡፡”
ወጣቱም ልጅ እንዲህ አለ “ምንም እይደል፣ እሷ ለእኔ በዚህ ¯KU ላይ ሁለ ነገሬ ናት ከብቶቼንም በሙሉ ይውሰዱ፡፡” በዚህም ሁኔታ ልጅቷን ማግባት ቻለ፡፡
ነገር ግን ምንም የሚመግባት ነገር ስላልነበረው አዳኝ በመሆን እሷንም መመገብ ቻለ፡፡
ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን የልጅቷ አባት ልጃቸውንና አማቻቸውን ሊጠይቋቸው ፈልገው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ በባህሉም መሰረት እንግዳ መጋበዝ ስላለበት ልጅቷ አባቷን ወደቤት አስገብታ እንዲቀመጡ ካደረገች በኋላ ውሃ ጥዳ ባሏ ያደነውን እንስሳ ይዞ እስኪመጣ መጠባበቅ ጀመረች፡፡ ነገር ግን ባሏ ሳይመጣ ውሃው ፈልቶ አለቀ፡፡ ተጨማሪ ውሃ ጨምራ ማፍላት ጀመረች፡፡ አሁንም ውሃው ተኖ አለቀ፡፡ እንደገና ማሰሮውን ሞልታ ማፍላት ጀመረች፡፡ አሁንም ውሃው ፈልቶ ተኖ አለቀ፡፡ ልጅቷም ተስፋ ቆርጣ ውጭ ውጭውን ማየት እንደጀመረች አንድ ሰው የገደለውን ድኩላ ይዞ በቤታቸው አጠገብ ሲያልፍ አየችው፡፡
ወደሰውየውም ጠጋ ብላ “እባክህ ጌታው ፣ አዳኝ የሆነው ባለቤቴ ወደ አደን ሄዶ ሳለ ያልጠበቅሁት እንግዳ ስለመጣብኝ እመግበው ዘንድ የድኩላውን አንድ እግር እባክህን ስጠኝና ለእንግዳው ምግብ ላቅርብለት ባለቤቴ ሲመለስ የወሰድኩትን ስጋ እመልስልሃለው፡፡” ብላ ተማፀነችው፡፤
እሱም “በፍፁም ስጋውን እንድትመልሽልኝ አልፈልግም፡፡ ለራሴ የሚበቃኝ ስጋ አለኝ፡፤ ስለዚህ ባልሽ የሚያመጣውን የእግር ስጋ አልፈልግም፡፡ ነገር ግን አንቺ በጣም ቆንጆ ስለሆንሽ ካንቺ ጋር መተኛት እፈልጋለው፡፡” አላት ፡፡
እሷም “እሺ፣ ነገር ግን አሁን እንግዳው በቤቴ ውስጥ ስላለ አሁን ሄደህ ወደ ማምሻው ላይ ተመልሰህ ና፡፡” አለችው፡፡
በዚህ ሁኔታ የእግር ስጋውን ወስዳ በመመለስ ማብሰል ጀመረች፡፡ ከዚያ በኋላ ባሏ የሜዳ አህያ ገድሎ ይዞ መጣ፡፡ እናም በጣም ብዙ ስጋ ስላገኙ ስጋውን ለሚስቱ ሰጥቷት ከአማቹ ጋር ተቀምጦ መመገብ ጀመረ፡፡
ቀኑም ሲመሻሽ ሌላኛው አዳኝ ተመልሶ በመምጣት ልጅቷ ሰምታው እንድትወጣ በሚል ጣሪያው ላይ ጠጠር ወረወረ፡፡ ነገር ግን እሷ ተቀምጣ የሜዳ አህያውን ስጋ ማብሰሏን ቀጠለች፡፡ አዳኙም ሁለተኛውን ጠጠር ወረወረ፡፡ ሆኖም ልጅቷ ያስተዋለች ባለመምሰል ዝም አለች፡፡ ሶስተኛውን ጠጠር ሲወረውር ልጅቷ ከት ብላ መሣቅ ጀመረች፡፡ በዚህ ግዜ አባቷ ዞር ብለው አይተዋት “ምንድነው እንዲህ የሚያስቅሽ?” ብለው ጠየቋት፡፡
እሷም ”የምስቀው በሶስት ጅሎች ነው፡፡” ብላ መለሰች፡፡ ቀጥላም “በሶስት ጅሎች ነው የምስቀው፡፡ አንደኛው ጅል ባለቤቴ ነው፡፡ ለሴት ሲል ሃብቱን በሙሉ አሳልፎ ሰጠ፡፡ ሁለተኛው ጅል አባቴ ነው፡፡ የገዛ ልጁንና የአማቹን ንብረት በሙሉ ወስዶ ሲያበቃ አብሮ ሊመገብ ይመጣል፡፡ ታዲያ ስጋው ከየት ይገኛል ብሎ ይጠብቃል? እና ሶስተኛው ጅል አሁን ውጭ የቆመው ሰውና የገደለውን ድኩላ አንድ እግር ስለሰጠኝ አብሬው እንድተኛ የሚፈልገው አዳኝ ነው፡፡” አለች ይባላል፡፡
የዚህ ተረት መልእክትም አንደኛው፣ወንዶች በሴትና በሃብት እንደሚታለሉ፣ ሁለተኛው ፣ ከፍቅር ባሻገር ሃብትም ሰዎች በደስታ እንዲኖሩ አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|