ሦስቱ መንገደኞች (ተጓዦች)
ተራኪው የማይታወቅ
ይህ ተረት ሶስት ሆነው ጉዞ ስለጀመሩ ሰዎች ይነግረናል፡፡ ረጅሙን ጉዞ በጀመሩ ጊዜ ለምግብነት የሚሆናቸውን አንድ ፍየል ያዙ፡፡ ፍየሏንም አንገቷን ቆርጠው ቆዳዋን ሳይገፉና ሳያጥቧት አንድ ቦታ ላይ ሲደርሱ ድንኳን ጥለው አረፍ አሉ፡፡ የታረደችውን ፍየል አጥበው ስጋውን መቀቀል ጀመሩ፡፡ ከሶስቱ ሰዎች ሁለቱ ሰዎች ረጃጅምና አንደኛው አጭር ነበሩ ሁለቱ ረጃጅሞች ታዲያ አጭሩን ሰው ይጠሉት ነበር፡፡ እናም አጭሩን ሰው ሊያሞኙት ወሰኑ፡፡
ስጋውንም ካበሰሉ በኋላ ረጃጅሞቹ እንዲህ አሉ “ሶስታችንም ስጋውን ከበላነው አይበቃንም፡፡ ስለዚህ አሁን እንተኛና ጥሩ ህልም ያየ ብቻ ይመገባል፡፡” በዚህም ግዜ ጥሩ ህልም አይተናል uTKƒ ስጋውን እንደሚበሉ ሁለቱ ረጃጅሞች አብረው አሴሩ፡፡ አጭሩ ሰው ሴራቸው ስለገባው በእቅዱ ተስማማ፡፡
“እንደዚያ ካላችሁ እኔም ፈጣሪዬ ጥሩ ህልም እንዲያሳየኝ እለምነዋለው፡፡” ብሎ ተኛ፡፡
ከዚያም ሁለቱ ረጃጅሞች ŸvÉ እንቅልፍ ውስጥ መሆናቸውን ሲያውቅ የተጠላው አጭር ሰው ተነስቶ ድስቱን በመክፈት ይበላ ጀመር፡፡ እስኪጠግብ ድረስም በላ፡፡ ከዚያም አጥንቱን ብቻ ወደ ማሰሮው መልሶ ማሰሮውን ከከደነ በኋላ ተመልሶ ተኛ፡፡ ከቆይታ በኋላም ሁለቱ ረጃጅም ሰዎች ተነስተው አጭሩን ሰው በመቀስቀስ ያዩትንም ያላዩትንም ጥሩ ህልም ይነግሩት ጀመር፡፡
አንደኛው እንዲህ አለ “ዛሬ ያየሁት ህልም ወደ አርሺ (ሰማይ ቤት) መሄዴን ነው፡፡ ፈጣሪዬን ሳወራው ቆየሁ፡፡”
ሁለተኛውም “ወደ መካ ሄጄ ነብዩ መሃመድን አግኝቼ ሳወራቸው ቆየG<፡፡” አለ፡፡
ሶስተኛውና አጭሩ ሰው “እንግዲህ ልጆች፣ በእኔ በኩል እንደናንተ አይነት ህልም አላየሁም፡፡ ሌሊት አንድ ወፍራም ጥቁር ባሪያ እግሩን አንገቴ ላይ ጭኖ ስጋዬን ሲበላ ነው ያደረው፡፡ ስለዚህ ምግቡን እንየው እስኪ፡፡” አላቸው፡፡
እናም ማሰሮው ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡
“ይህማ ህልም አይደለም፡፡” አሉ፡፡ “ይህ እውነት ነው፡፡ ሰውየው ስጋውን ሲበላ ለምን አልቀሰቀስከንም?” ብለው ሲጠይቁት አጭሩም ሰው እንዴት? በዚያን ግዜ ከየት ላግኛችሁ አንደኛችሁ ወደ ገነት ሄዶ ከፈጣሪው ጋር ሲያወራ ነበር፣ ሌላኛችሁ ወደ መካ ሄዶ ከነብዩ መሃመድ ጋር ሲነጋገር ነበር፡፡ ስለዚህ ላገኛችሁ አልቻልኩም ነበር፡፡” አላቸው፡፡
በዚህም በጣም ተበሳጭተው ምንም ነገር ሳይበሉ ተኙ፡፡
በሁለተኛው ቀን ለእለቱ የያዙትን ምግብ በሉ፡፡ ሆኖም ቁጭት አድሮባቸው ስለነበር አጭሩን ሰው ሊያታልሉት አሴሩ፡፡ በእንቅልፍ ላይ ሳለም እሣት ለኩሰው ብርድልብሱንና የሳር ፍራሹን በማቃጠል ሊቀጡት ወሰኑ፡፡ ሆኖም አጭሩ ሰው በሚስጥር ያልሰማና ያላየ በመምሰል እሳቱን ቀስ ብሎ አጠፋው፡፡ ሁሉንም ነገር ችሎ ፀጥ ብሎ ቆየ፡፡ ሌሎቹም ስራቸውን ጨርሰው ሲተኙ እሱ ተነስቶ የአህዮቹን የላይኛውንና የታችኛውን ከንፈሮች በመቁረጥና ድዳቸው እንዲታይ በማድረግ የሚስቁ አስመስሏቸው ተኛ፡፡
በማግስቱ ጠዋት ሁለቱ ሰዎች ተነስተው “አንተ መጥፎ ሰው! አንተ ላይ ባለው እርግማን ምክንያት እሳት ከሰማይ ወርዶ ሲያቃጥልህ እኛንም አቃጥሎን ነበር፡፡ ተነስ አሁን! ተነስ!” ብለው ጮሁበት፡፡ እሱም “ምንድነው የምትሉት? ለዚህ ነው አህዮቻችሁም በእኔ መቃጠል እየሳቁ ያሉት?” አላቸው ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|