መነሻ ትግራይ
ትግራይ
ተረቶቹ የተሰበሰቡት በክልሉ ርዕሰ ከተማ በመቀሌ በመጋቢት 1989 ዓ.ም. በአቶ ኣታክልቲ ሃጋግ አመራር ሥር በነበረው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባልደረባ በአቶ መለሰ ዘለቀ እገዛ ነበር፡፡ ከሌሎቹ ክልሎች በተለየ መልኩ በዚህ ክልል ለፕሮጀክቱ ሲባል ምንም አይነት ተረት ለኤልሳቤት ላያርድ በቀጥታ አልተተረከም፡፡ ከዚህ በፊት መሰለ ዘለቀ በጸሃይነሽ ገብረዮሃንስ የተከናወነ አንድ የተረት ማሰባሰብ ፕሮጀክት ነድፎ ነበር፡፡ ተማሪዎች በታላላቆቻቸው የተነገሩአቸውን ተረቶች ጽፈው ለትምህርት ቢሮው እንዲልኩ ከተደረገው የተረቶች ስብስብ ውስጥ ወይዘሮ ጸሃይነሽና አቶ መሰለ የተወሰኑትን ወደ አማርኛ በመመለስ ለንብቡ ፕሮጀክት እንዲሆን በማድረግ መልካም ትብብራቸውን ለግሰዋል፡፡ በኤልሳቤት ላያርድ ጉብኝት ወቅት ተረቶቹን የጻፉት ልጆች ስም ስላልተመዘገበ እዚህም ማስፈር አልተቻለም፡፡ የትግራይ ገበሬ በእርሻ ሥራ ላይ በዚህ መልኩ የተገኙት ተረቶች (በትግራይ) በተማሪዎች የተጻፉ ሲሆኑ የተወሰኑት ተማሪዎች ከሌሎቹ በተሻለና ምሉዕ በሆነ መልኩ ስለጻፉ አንዳንዶቹ ተረቶች የማጠቃለያነት ባህሪይ አላቸው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የመደበኛ ተረት ተናጋሪ ሰው ድምጸትና አድማጩን የሚያማልልበት ቅላጼና የአነጋገር ውበት ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይዘት፡:
|