ጅብ፣ ቀበሮና ጦጣ 2
ተራኪው የማይታወቅ
ጅብ፣ ቀበሮና ጦጣ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን አራት ላሞችን በመንደሩ ካለው አንድ ቤት ሰረቁ፡፡ እያንዳንዳቸው አንድ፣ አንድ ላም ከተካፈሉ በኋላ “አራተኛዋን ላም እንዴት እናድርጋት” ብለው ተወያዩባት፡፡
ከዚያም “አራተኛዋን ከሁላችንም በእድሜ አንጋፋ የሆነው ይውሰዳት፡፡” አሉ፡፡
በዚህም ከተስማሙ በኋላ ጅቡን “መች ነው የተወለድከው?” ብለው ሲጠይቁት “አምናና ካቻምና፡፡” አላቸው፡፡
ጦጣውም “እኔ የተወለድኩት ሰማይና ምድር ሲፈጠሩ ነው፡፡” አለ፡፡ ቀበሮዋም “ትክክል ነው፡፡ አስታውሳለሁ፡፡ አንድ ሽበታም ሰው መወለዱን ሰምቼ በድግሱ ላይ ተሳትፌ የስንዴ ገንፎ፣ ኬክ በቅቤና በርበሬበርበሬ በጣም የሚያቃጥል የኢትዮጵያ ቅመም ነው፡፡ በጌሎፑ ላይ በልቻለሁ፡፡” አለች፡፡ (ጌሎፕ ልጅ ከተወለደ ከሰባተኛው ቀን በኋላ የሚደረግ የልብስ አጠባ ስርአት ነው፡፡)
“እና አንጋፋው ማነው?”
ቀበሮዋ፡፡
እናም እርሷ አራተኛዋን ላም ወሰደች፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|