ብልኋ እናትና ብልህ ሴት ልጇ
ተራኪው የማይታወቅ
እርስ በርስ የማይተዋወቁ ሁለት ሰዎች ነበሩ፡፡ መንገድ ላይም ተገናኝተው አብረው መጓዝ ጀመሩ፡፡
አንደኛው ሰው “አንተ ሰው፣ ወይ አንተ እዘለኝ ወይም እኔ ልዘልህ፡፡” ሲለው ሌላኛው ሰው ግራ ገብቶች “እንዴት ከባድ ሰው ሌላውን ከባድ ሰው ሊሸከም ይችላል?” በማለት ዝም አለው፡፡
ሌላኛው ሰው ግን አሁንም “እኔ ትንሿን ጣቴን ልስጥህና አንተ አውራ ጣትህን ስጠኝ፡፡” አለው፡፡ (ይህ ማለት ሴት ልጄን ለወንድ ልጅህ ልዳርለት ወይም ያንተን ሴት ልጅ ወንድ ልጄ ያግባት ማለት ነበር፡፡)
ሁለተኛው ሰው ግን “ይህ ምን አይነት ሰው ነው?” ብሎ አጉተመተመ፡፡ (ነገሩ አልገባውም ነበር፡፡)
በመጨረሻም ሲለያዩ ጠያቂው ሰው “ለጥያቄዎቼ መልስ ስጠኝና እንደዚህ፣ እንደዚህ ከሚባል ቦታ እንገናኝ፡፡” አለው፡፡
ሁለተኛውም ሰው አሁንም “ይህ ምን አይነት ሰው ነው?” ብሎ አስቦ ምንም ሳይናገር ወደቤቱ ሄዶ ስለሆነው ነገር ለቤተሰቡ አጫወታቸው፡፡
ግራ የሆነ ሰው እንዳጋጠመውና ያልሆኑ ጥያቄዎችን ጠይቆት መልስ ይዘህ ና እንዳለው ነገራቸው፡፡
የሰውየውም ቤተሰብ የመጀመሪያው ጥያቄ አንተ ተረት ንገረኝ ወይም እኔ ልንገርህ ማለት እንደሆነና ሁለተኛውም ጥያቄ ልጆቻችንን እናጋባ ማለት እንደሆነ ነገሩት፡፡
ሚስቱም “ሰውየው ጋ ተመልሰህ ስትሄድ ‘እኔ ትንሿን ጣቴን እሰጥሃለሁ’ በለው፡፡” አለችው፡፡
ሰውየውም “እሺ” ብሎ በመሄድ “ትንሿን ጣቴን እሰጥሃለሁ፡፡” አለው፡፡ በዚህም ተስማምተው ጋብቻው ተፈፀመ፡፡ የሙሽራው ቤተሰብ ሙሽራዋን ሊወስዱ ሲመጡ የሙሽራው አባት የሙሽራዋን ቤተሰብ “አዳምጡኝ፣ ሙሽራዋን ዛሬ የምንወስዳት ከሆነ ወንድ ልጅ መውለድ አለባት፣ አለበለዚያ አንወስዳትም፡፡” አሉ፡፡
የሙሽራዋም አባት “ይህ ምን አይነት ሰው ነው? አብዷል እንዴ?” ብለው አሰቡ፡፡ ሆኖም ወደ ልጃቸው ሄደው የተጠየቁትን ነገሯት፡፡ ልጅቷም “እሺ በላቸው፡፡” አለቻቸው፡፡
በዚህ ሁኔታ ሙሽራዋን ወስደው ወደ ሙሽራው ቤት ስትሄድ በቀሚሷ ስር እንዳይርባት የታጠቀችው መቀነት ነበር፡፡
እነርሱም “መቀነትሽን ፈትተሸ እንጀራእንጀራ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች ከሚበቅለው ጤፍ የተባለ ሰብል የሚሰራ ጠፍጣፋ፣ ስስና ክብ ምግብ ነው፡፡” ብዪ፡፡” አሏት፡፡
እርሷ ግን እምቢ አለች፡፡
የሙሽራውም አባት “ለምንድነው የማትበይው?” አሏት፡፡
እርሷም “ዛሬ የጋብቻዬ ቀን ስለሆነ ወንድ ልጅ መውለድ ካለብኝ ዛሬ ተዘርቶ፣ ዛሬ በቅሎ፣ ዛሬ የታጨደ እህል ነው መብላት ያለብኝ፡፡ አለበለዚያ አልተኛም፡፡” አለች፡፡
የሙሽራውም አባት መልስ አጡ፡፡
በመጨረሻም “ይህቺ ልጅ ብለህ ናት፡፡ ያስቀመጥናቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ሁሉ እናንሳ፡፡” አሉ፡፡
ተጋቢዎቹም በደስታ ኖሩ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|