ቀበሮና ቁራ
ተራኪው የማይታወቅ
አንዲት ቀበሮ ደጇ ላይ ጥራጥሬዎች፣ ስንዴ፣ ጤፍጤፍ በኢትዮጵያ ደጋማ ስፍራዎች የሚበቅል ሰብል ነው፡፡ ወይም ማሽላ አስጥታ ስታደርቅ አንድ ቁራ መጥቶ ይለቅምባት ጀመር፡፡ ቀበሮዋም ቁራውን ልትይዘው ብትሞክር እየበረረ ያመልጣታል፡፡
ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን ቁራው በአንድ ጉዳና ላይ ሲራመድ አግኝታው ቀበሮዋ ከያዘችው በኋላ “እህሌን እየበላህ የምታስቸግረኝ ለምንድነው?” አለችው፡፡
ቁራውም “የፈለግሺውን ነገር ልታደርጊኝ ትችያለሽ፡፡ ነገር ግን እባክሽ ወደ ቁጥቋጦው ውስጥ አትወርውሪኝ፡፡” አላት፡፡
ቀበሮዋም “ቁጥቋጦው ውስጥ ብወረውረው ይሞታል፡፡” ብላ ስትወረውረው ቁራው በርሮ ሄደ፡፡
ከበረረም በኋላ “አንቺ ጅል! አታለልኩሽ!” አላት፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|