በግና ፍየል
ተራኪው የማይታወቅ
አንዲት በግና አንዲት ፍየል መስኩ ላይ ሳር ይግጡ ነበር፡፡ በጓም ፍየሏን “ወደቤታችን እንሂድ፡፡” አለቻት፡፡
ፍየሏ ግን “ለምን? እኔ መጋጥ እፈልጋለሁ፡፡” አለቻት፡፡ በጓ ግን ስለበረዳት “ዋሻው ውስጥ ለምን አልገባም?” ብላ ወደ አንዲት ቀበሮ ዋሻ ገብታ መሞቅ ጀመረች፡፡
በዚህ ግዜ አንዲት ጥንቸል መጥታ “በቀበሮዋ ቤት ውስጥ ያለው ማነው?” ብላ ስትጠይቅ በጓም እኔ የተጠጋኝን ሁሉ በጭንቅላቴ የምመታው በግ ነኝ፡፡” አለች፡፡
ጥንቸሏም ፈርታ ሄደች፡፡
ጅቡም መጥቶ “በቀበሮዋ ቤት ውስጥ ያለው ማነው?” ሲል አሁንም በጓ “እኔ የተጠጋኝን ሁሉ በጭንቅላቴ የምመታው በግ ነኝ፡፡” አለችው፡፡ ጅቡም ፈርቶ ሸሸ፡፡
ቀበሮዋም መጥታ ተመሳሳይ ጥያቄ ስትጠይቅ በጓም ተመሳሳይ መልስ ስለሰጠቻት ሮጣ ተመለሰች፡፡ ከዚያም ቀበሮዋ ጅቡን ምን ማድረግ እንዳለባት ስትጠይቀው ጅቡም “ወደ ዋሻው ሄደሽ ‘በግ ሆይ፣ ገረድሽ መሆን እችላለሁ’ በያት አላት፡፡ ቀበሮዋም እንደተባለችው ሄዳ በጓን “ገብቼ ገረድሽ ልሁን?” ብላ ስትጠይቃት በጓም “እሺ” ብላ ስትከፍት ቀበሮዋ ገብታ ገደለቻት፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|