አንዲት ሴትና አያ ጅቦ
ተራኪው የማይታወቅ
አንዲት ብቻዋን የምትኖር ደካማ ሴት ነበረች፡፡ ታዲያ አንድ ቀን በቀን በሯን ሳትዘጋ ተኝታ በዚያው ስለመሸ ሌሊት አያ ጅቦ መጥቶ እስከ ተጠቀለለችበት ቁርበት ይዟት ሄዶ ከአንድ ጥግ ካስቀመጣት በኋላ ጓደኞቹን ሊጠራ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ሴትየዋ ከእንቅልፏ ነቅታ ቤቷ አለመሆኗን ስታውቅ በጣም ፈራች፡፡ ከዚያም ቁርበቱን ሰው እንዳለበት አስመስላ ጠቅልላው ሮጣ ሄደች፡፡
ቤቷም በደረሰች ጊዜ በሯን ዘግታ እንደገና ተኛች፡፡ ጅቡም ከጓደኞቹ ጋር ተመልሶ ሲመጣ ቁርበቱን ተጠቅልሎ ስላገኘው ሴትየዋ ያለች መስሎት ሲነካው ሴትየዋ ሄዳለች፡፡
በዚህ በጣም ተበሳጭቶ ወደ ሴትየዋ ቤት ተመልሶ ሲሄድ በሯ ዝግ ሆኖ ስላገኘው ወደ ጓደኞቹ ተመልሶ ሄደ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|