የአንዲት ሴት አስቸጋሪ ቡችላ
ተራኪው የማይታወቅ
አንዲት ቃዚት የተባለች ቡችላ የነበራት ሴት ነበረች፡፡ ቡችላዋ ታዲያ ቤት ውስጥ ያገኘችውን ምግብ ሁሉ ትበላ ስለነበረ ሴትየዋ በሌባዋ ቡችላ በጣም ትናደድ ነበር፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ሴትየዋ ቡችላዋን ሙቀጫ ውስጥ አስቀምጣ ዘነዘና ልታመጣ ስትሄድ ቡችላዋ ነገሩ ገብቷት ከሙቀጫው ውስጥ ዘላ በመውጣት የሴትየዋን ህፃን ልጅ ወስዳ ሙቀጫው ውስጥ ከተተችው፡፡
ሴትየዋም የራሷን ልጅ ወቅጣ ስትገድለው ቡችላዋ በሩቅ ሆና እየተመለከተች “ተበቀልኩሽ” አለቻት፡፡
በታሪኩ መጨረሻ ላይ ተራኪው እንዲህ ይላል፤
“አነ ቃዚት
ትበል ላሲት፡፡”
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|