የአውቶብሱ ጉዞ
ተራኪው የማይታወቅ
በአንድ የገጠር አካባቢ የሚኖር በጣም መሃይም ሰው ወደ ሩቅ አገር መሄድ ፈልጎ ጓደኛውን “እንዴት ነው መሄድ የምችለው? በጣም ሩቅ ነው፡፡” አለው፡፡
ጓደኛውም “ለምን በአውቶብስ አትሄድም” ሲለው ሰውየውም “አውቶብስ ምን እንደሚመስል አላውቅም፡”፡ አለው፡፡
ጓደኛው “አውቶብስ ከፊት ለፊቱ መስታወት ያለው ሲሆን አውቶብሱ ሲመጣ ገንዘብ ከፍለህ ከገባህ በኋላ ካርኒ ተቀብለህ መጓዝ ብቻ ነው፡፡” ብሎ ነገረው፡፡
ሰውየውም አውቶብሱን ሲሳፈር አውቶብሱ ውስጥ ሌላ መነፅር ያደረገ ሰው አይቶ ጓደኛው የነገረውን ስላስታወሰ መነፅሩ መስታወት መስሎት መነፅር ያደረገው ሰውዬ ላይ ተቀመጠ፡፡ ባለመነፅሩም “ምን አባክ እያደረክ ነው? ሂድ ከዚህ፡፡” ሲለው በዚህ ተጣልተው ወደ ዳኛ ለመሄድ ወሰኑ፡፡
መሃይሙም ሰው “ካርኒውን ስለገዛሁ መስታወቱ ጋ መቀመጥ አለብኝ፡፡” አለ፡፡
ዳኛውም “ከገጠር ስለመጣ አያውቅምና ተወው፡፡” ብሎ በነፃ ለቀቀው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|