ቀበሮና ዶሮ
ተራኪው የማይታወቅ
ከእለታት አንድ ቀን አንድ ቀበሮ አንዲት ቆንጆ ዶሮ አይቶ ዶሮዋን ከምትኖርበት አውጥቶ ወደቤቱ ሊወስዳት ፈለገ፡፡ በመሸ ጊዜም ዶሮዋን ከረጢት ውስጥ ከቷት ወደ ቤቱ እየተጓዘ ሳለ እንቅልፍ ያዘው፡፡
ቀበሮውም በተኛ ጊዜ ዶሮዋ ቀስ ብላ ከከረጢቱ በመውጣት ከረጢቱ ውስጥ ድንጋይ አኑራ ወደ ቤቷ እየሮጠች ሄደች፡፡ ቀበሮው ከእንቅልፉ ሲነቃ ድንጋዩን በከረጢት ተሸክሞ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ቤቱ ሲደርስ ግን ከረጢቱ ውስጥ ያገኘው ድንጋይ ነበር፡፡ ከረጢቱን ከመፍታቱ በፊት ግን ዶሮዋን ማብሰያ ውሃ አፍልቶ ሲያበቃ ወደ ከረጢቱ ሄዶ ሲፈታው ያገኘው ድንጋይ በመሆኑ በጣም ተናደደ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|