ጦጣዎቹና ዝንጀሮዎቹ
ተራኪው የማይታወቅ
ጦጣዎች የገብስ ጥሬ ይበሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ዝንጀሮውን ገብሱ አጠገብ ስለማያደርሱት ስለተናደደ “እነዚህን ጦጣዎች እንዴት ልጎዳቸው እችላለሁ” ብሎ አሰበ፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ዝንጀሮው ከዛፎች ላይ ወጥቶ በገና መጫወት ጀመረ፡፡ ዝንጀሮውም የሙዚቃውን መሳሪያ ሲጫወት የሰማው አንበሳ ለእርሱም እንደዚህ ያለ የሙዚቃ መሳሪያ እንዲሰራለት ጠየቀው፡፡
ዝንጀሮውም “እንደዚህ አይነት በገና እንድሰራልህ ከፈለክ ክሮች ያስፈልጉኛልና ክሮቹ ከጦጣ ቆዳ የተሰሩ መሆን አለባቸው፡፡” አለው፡፡
አንበሳውም ጦጣዎቹን በሙሉ ገድሎ ቆዳቸውን ለዝንጀሮው ሰጠው፡፡ ዝንጀሮውም አንበሳው ቆዳዎቹን ወደ ወንዝ ወስዶ እንዲያጥባቸው ነገረው፡፡ አንበሳውም ቆዳዎቹን እያጠበ ሳለ ዝንጀሮው ከኋላ መጥቶ አንበሳውን ውሃው ውስጥ ገፍትሮ ሲጥለው አንበሳው ተደፍቆ ሞተ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|