ዝንጀሮ፣ ጅብና ተኩላ
ተራኪው የማይታወቅ
ዝንጀሮ፣ ጅብና ተኩላ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ጅብና ተኩላውም ፍየል ለማደን ወደ አንድ ሩቅ ስፍራ ሲሄዱ ዝንጀሮው ግን በጩኸቱ ስላስደነበራቸው ፍየሎቹ ሁሉ ሸሹ፡፡ ጅቡና ተኩላውም ነፃ ይሆኑ ዘንድ ዝንጀሮውን ሊገድሉት ወሰኑ፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ወደ አንበሳው በመሄድ ዝንጀሮው ያደረጋቸውን ነገር ነግረውት “ጌታዬ ሆይ፣ አንተም ብትሆን ጫማ የለህምና ዝንጀሮው ጫማ እንዲሰራልህ ለምን አትጠይቀውም?” አሉት፡፡
አንበሳውም በሃሳቡ ተስማምቶ ዝንጀሮው ጫማ እንዲሰራለት ጠየቀው፡፡
ዝንጀሮውም “እሺ፣ ጫማዎቹን መስራት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን የጅብና የተኩላ ቆዳ ያስፈልገኛል፡፡” አለው፡፡
አንበሳውም ጅቡንና ተኩላውን ገድሏቸው ዝንጀሮው ነፃ ሆነ፡፡ በመጨረሻም ዝንጀሮው አንበሳውን “በል አሁን ደማቸውን ውሃው ውስጥ እጠበው፡፡” ብሎት አንበሳው ሊያጥብ ጎንበስ ሲል ገፍትሮ ሃይቁ ውስጥ ከተተው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|