ሲድሮምና እህቶቹ
ተራኪው የማይታወቅ
አንዲት ሶስት ሞኞችና ረጃጅም ሴት ልጆቸ የነበሯት ሴት ነበረች፡፡ ልጆቿም በሙሉ ሞኞች እንደሆኑ ስታውቅ እግዜር ድንክም እንኳን ብትሆን አንዲት ብልጥ ልጅ እንዲሰጣት ለመነች፡፡ እግዜርም ፀሎቷን ሰምቶ አንድ ድንክ ወንድ ልጅ ሰጣት፡፡ ስሙንም ሲድሮም (ድንክ) ብላ ጠራችው፡፡ ሲድሮም በጣም ተንኮለኛና የሚገርም ልጅ ነበር፡፡ ለሞኝ እህቶቹም በጣም አስቸጋሪ ሆነባቸው፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ሁሉም ተኝተው ሳለ ክፍላቸው ውስጥ ቀስ ብሎ በመስኮት ገብቶ ገንዘባቸውን ሁሉ ሰረቀባቸው፡፡ ይህንንም ባወቁ ጊዜ ከሚስቱና ከወንድ ልጁ ጋር በቤቱ ውስጥ እንዳለ ሊያቃጥሉት አቀዱ፡፡ ይህንን ሲያቅዱ ታዲያ ሲድሮም ሰምቷቸው ሶስት መራር ፍሬዎችን በቤቱ ውስጥ አስቀምጦ ልጁንና ሚስቱን ይዞ ሄደ፡፡ እህቶቹም ቤቱን ሲያቃጥሉ ፍሬዎቹ ፈነዱ፡፡
እህቶቹ ታዲያ አንዱ ፍሬ ሲፈነዳ “አሃ! ይሄ ሲድሮም ነው፡፡” ሲሉ ሁለተኛውም ሲፈነዳ “ይህቺ ደግሞ ሚስቱ ናት፡፡” እያሉ ሶስተኛውንም “ይህ ደግሞ ልጁ ነው፡፡” በማለት ሶስቱም እንደሞቱ ገመቱ፡፡
ሲድሮም ታዲያ የተቃጠለውን ቤት አመድ በከረጢት ውስጥ አድርጎ ይዞ ሄደ፡፡
በማለዳም በጉዞው ላይ ሳለ አንድ ጊዜ ሲጮህ ጎረቤቱቹ ሁሉ ሮጠው ወጥተው “ምንድነው ነገሩ?” አሉ፡፡
እርሱም “ነጩ ጤፌ ወደ አመድነት ተቀየረ፡፡” ብሎ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡
ሰዎቹም “በል እሺ ዝም በልና እኛ ጤፉን እንሰጥሃለን፡፡” አሉት፡፡
ከረጢቶቹንም በጤፍ ሞልተውለት ወደ አዲሱ ቤቱ ሄዶ ዘመዶቹን ሲያገኛቸው “ቤቴን ስላቃጠላችሁብኝ አመዱን በነጭጤፍ ለወጥኩት፡፤” አላቸው፡፡ እነርሱም ቤታቸውን አቃጥለው አመዱን በከረጢት ሞልተው “አመድ በነጭ ጤፍ የሚለውጥ” እያሉ ይዞሩ ጀመር፡፡ ሆኖም ሰው ሁሉ ስቆባቸው ወደቤታቸው ተመለሱ፡፡ ከዚያም ሲድሮምን ሊገድሉት አቀዱ፡፡
ሲድሮምም ሚስቱን “አንድ ባዶ የጠላ ማሰሮማሰሮ ጠላ መጥመቂያ ነው፡፡ አዘጋጂና አጥብቀሽ እሰሪው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንድ የሸክላ ድስትና ባዶ እንስራ አዘጋጅተሽ በቆንጆ ሽፋን ከድነሽ አክንባሎ ያለው የእንጀራእንጀራ በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች ከሚበቅለው ጤፍ የተባለ ሰብል የሚሰራ ጠፍጣፋ፣ ስስና ክብ ምግብ ነው፡፡ ምጣድ አብረሽ አስቀምጪ፡፡” አላት፡፡
ሲድሮም ይህን ካለ በኋላ ቤታቸውን ወዳቃጠሉት ዘመዶቹ ቤት ሊጠራቸው ሲሄድ እነርሱ ደግሞ ሊገድሉት እየመጡ ስለነበረ መንገድ ላይ ተገናኙ፡፡
እርሱም “ወደእኔ ቤት ኑና ሃይማኖታዊውን ድግስ ተካፈሉ፡፡” አላቸው፡፡
ዘመዶቹም ወደ ሲድሮም ቤት በሄዱ ጊዜ እቃዎቹ ሁሉ ባዶ ሆነው አገኟቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሲድሮም ያበደ መስሎ ቢላዋ በማንሳት በደነዙ ጠርዝ ሚስቱን የሚያርዳት ሲመስል እርሷም የሞተች መስላ ከዚያ በኋላ ነቃች፡፡
ዘመዶቹም ይህንን ሲያዩ ተገርመው “እኛም ሚስቶቻችንን እንደዚህ ማድረግ አለብን፡፡” ተባብለው ወደየቤታቸው በመሄድ የሚስቶቻቸውን አንገት በቢላዋ ከቆረጡ በኋላ “ተነሽ!” ቢሏቸው ሚስቶቻቸው ሞተው ነበር፡፡
ሲድሮምም ወደዘመዶቹ ቤት ሲሄድ የሞቱትን ሚስቶች ባየ ጊዜ ሰዎቹ “እኛም እንዳንተ ነበር ያደረግነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ አልነቃ አሉ፡፡” ብለው ነገሩት፡፡
እርሱም “ጭንቅላታቸውን በጥሳችሁ ጥላችሁታላ!” አላቸው፡፡
በዚህ ጊዜ በጣም ስለተረበሹ “ሃይቁ ውስጥ እንጣለው፡፡” ተባብለው በትልቅ ሳጥን ውስጥ ከተውት ሲሄዱ ሲድሮም ውስጥ ሆኖ “ቁርሳችሁን ካልበላችሁ በረሃብ ትሞታላችሁ፡፡” አላቸው፡፡
እነርሱም በሃይቁ ዳርቻ ላይ አስቀምጠውት ቁርሳቸውን ሊበሉ ሄዱ፡፡ በዚህ ጊዜ በስፍራው ያልፉ የነበሩ አንድ ቄስ ሳጥኑን አይተው ሲከፍቱት ሲድሮምን ውስጡ አገኙት፡፡
ቄሱም “እዚህ ምን እያደረክ ነው?” ብለው ሲጠይቁት ሲድሮምም “ሞቼ ገነት መግባት እፈልጋለሁ፡፡” አላቸው፡፡
ቄሱም ፈረሳቸውን ሰጥተውት “አይሆንም፣ እኔ ሳጥኑ ውስጥ ልግባና ገነትን ልውረስ፡፡” አሉት፡፡
ሲድሮም ሲመለስ ዘመዶቹ አግኝተውት “ምን እየሰራህ ነው?” ብለው ሲጠይቁት “እናንተ ሃይቁ ውስጥ ልትከቱኝ ስታቅዱ እኔም ሃይቁ ውስጥ ገብቼ ፈረስ ይዤ መጣሁ፡፡” አላቸው፡፡
እነርሱም ፈረሱን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ሲጠይቁት ወደ ሃይቁ ዳርቻ ወስዷቸው ፈረሱን ሃይቁ አፋፍ ላይ ሲያቆመው የፈረሱን ምስል ውሃው ውስጥ አይተው ሃይቁ ውስጥ ዘለው ገብተው ሞቱ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|