የዱር ፍሬ
ተራኪው የማይታወቅ
አንድ እረኛ ሁልጊዜ ከብቶቹን ወደ ወንዙ ውሃ ሊያጠጣቸው ቢሄድም በፍጹም እንዲጠጡ አድርጎ አያውቅም፡፡ የክብቶቹም ባለቤት ከብቶቹን ሲያያቸው ደህና ስላልመሰሉት መጠራጠር ጀመረ፡፡ እናም ከእለታት አንድ ቀን ባለቤቱ ከከብቶቹ ጋር ሲሄድ ከብቶቹ በውሃ ጥም አብደው ስለነበር ያለልክ ስለጠጡ ውሃው በዝቶባቸው ሞቱ፡፡
ሰውየውም እረኛውን ሲገርፈው እረኛው በግጥም እንዲህ አለ፤
“የዱር ፍሬ፣ የዱር ፍሬ
እየፈለኩሽ ነበር
ሁልጊዜ ማታ ማታ በዚህ ምክንያት እገረፍ ነበር፡፡”
በመጨረሻም የከብቶቹ ባለቤት እረኛውን ደብድቦ ገደለው፡፡
< ወደኋላ |
---|