ተገኘ
ተራኪው የማይታወቅ
በአንድ ወቅት አንድ አዛውንት ሰው ልብሳቸውን ለማጠብ ወደ ወንዝ እየወረዱ ሳለ አንድ ወንድ ልጅ በመንገዱ ላይ አገኙ፡፡
ልጁም “ወዴት እየሄዱ ነው፣ አባቴ?” ብሎ ሲጠይቃቸው አዛውንቱም ሰው “ልብሶቼን ላጥብ ወደ ወንዙ እየሄድኩ ነው፡፡” ብለው መለሱ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ “ልብሶችዎን እኔ ለምን አላጥብልዎትም?” ሲላቸው አዛውንቱ ሰው እሺ ብለው የልጁን ስም ጠየቁት፡፡
ልጁም “ስሜ ተገኘ ነው፡፡” አላቸው፡፡
አዛውንቱም ሰው ከልጁ ጋ ልብሳቸውን ተመልሰው የሚወስዱበትን ሰአት ተቃጥረው ሄዱ፡፡ ሆኖም ልጁ በቀጠሮው ሰአት አልተገኘም፡፡ የአዛውንቱ ሰው ጓደኞች አዛውንቱን ሲያይዋቸው ለምን እዚያ እንደተቀመጡ ጠየቋቸው፡፡
አዛውንቱም ሰውዬ “ልብሶቼን ሊያጥብልኝ ወደ ወንዙ ይዞ የሄደውን ልጅ እየጠበኩ ነው፡፡” አሏቸው፡፡ ሰዎቹም ልጁን ያፋልጓቸው ዘንድ እርዳታቸውን ጠየቁ፡፡
ሰዎቹም “ተገኘ! አለህ?” እያሉ ሲፈልጉ አዛውንቱ ሰው ልብሳቸው የተገኘ መስሏቸው ወደቤታቸው ሄዱ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|