ጎበዟ ሴት
ተራኪው የማይታወቅ
በአንድ ወቅት ሁለት ጓደኞች ነበሩ፡፡ አንደኛው በጣም ብሩህ አእምሮ ያለው ሲሆን ሌላኛው መሃይም ነበር፡፡ ሁለቱም ትዳር የነበራቸው ሲሆን የጎበዙ ሰው ሚስት መሃይም ነበረች፡፡ መሃይሙ ሰው ደግሞ ጎበዝ ሚስት ነበረው፡፡
ጎበዙም ሰው ጓደኛውን “ሚስትህ ላንተ አትሆንም፡፡ ያንተን ሚስት ስጠኝና የእኔን እሰጥሃለሁ፡፡ ምክንያቱም ሚስትህ በጣም ጎበዝ ስትሆን እኔም ጎበዝ ነኝ፡፡” አለው፡፡
መሃይሙም ሰው “አንተ የምታውቀውን እኔም አውቃለሁ፡፡ እኔም እንዳንተ ጎበዝ ነኝ፡፡ ይህንን እንዴት ልትል ቻልክ?” አለው፡፡
ጎበዙም ሰው “በዳኛ ፊት እኔ የማውቀውን ካወቅህ ያንተ ሚስት የራስህ ትሆናለች፡፡ አለበለዚያ ግን እንቀያየራለን፡፡” ሲለው በዚህ ተስማምተው ወደ ዳኛ ዘንድ ሄዱ፡፡
መሃይሙም ሰው “በል እንግዲህ ጠይቀኝ፡፡” አለ፡፡
ጎበዙም ሰው “የኮከቦች ብዛት ስንት ነው? የምድርስ እምብርት የት ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡
መሃይሙም ሰው ስለተደናገረው ዳኛው “ትንሽ ጊዜ ወስደህ ወይም ለቀናት አስብበት፡፡” አለው፡፡
ወደየቤታቸውም ተመለሱ፡፡
መሃይሙ ሰው የቤቱ ጣሪያ ላይ ወጥቶ ኮከቦቹን ለመቁጠር ሲሞክር ብዙ ጊዜ አባከነ፡፡
በዚህ ጊዜ ሚስቱ “ና ውረድ፡፡ ምን እያደረክ ነው? ምን ሆነሃል?” ስትለው ጉዳዩን አጫወታት፡፡
እርሷም “በል ና ውረድ፡፡ መልሱን እኔ እነግርሃለሁ፡፡” አለችው፡፡
ወደ ዳኛው የሚመለሱበትም ቀን በደረሰ ጊዜ መሃይሙ ሰው “ምን ልበል?” ብሎ ሚስቱን ጠየቃት፡፡
ሚስቱም “በአንዲት ትንሽ ከረጢት ጤፍናጤፍ በኢትዮጵያ ደጋማ ስፍራዎች የሚበቅል ሰብል ነው፡፡ ጫፉ ላይ ጦር የተሰካበት ዘንግ ይዘህ ሄደህ ሰውየው ጥያቄውን ሲጠይቅህ ‘የኮከቦቹ ቁጥር ከረጢቱ ውስጥ ያሉትን የጤፍ ቅንጣቶች ቁጥር ያህላል’ ብለህ መልስለት፡፡ ካላመነህ የጤፉን ዘሮች እንዲቆጥራቸው ንገረው፡፡ የምድርም እምብርት የት እንደሆነ ሲጠይቅህ ጦሩን መሬት ላይ ሰካውና ‘ይህ እምብርቱ ነው፡፡’ በለው፡፡ ካላመኑህ እንዲቆፍሩ ንገራቸው፡፡” አለችው፡፡
እርሱም እንደተባለው አደረገ፡፡
ዳኛውም “እነዚህን መልሶች የነገረህ ማነው?” ብሎ ሲጠይቀው “ሚስቴ” ብሎ መለሰ፡፡
ከዚያም ዳኛው “ይህች ሰው ላንተ አትገባህም፡፡ በጣም ብልህ ናትና ትታህ መሄድ አለባት፡፡” ብሎ ፈረደ፡፡
ምስኪኑም ሰው በጣም ስጋት ያዘው፡፡
ሚስቱም “ምን ሆንክ?” ስትለው “አሸነፍኩ፣ ግን አሁንም ሊወስዱሽ ይፈልጋሉ፡፡” አላት፡፡
ሚስቱም “አታስብ፣ እስኪ እንጠብቅ፡፡” አለችው፡፡ ወደ ዳኛው መመለሻቸውም ቀን በደረሰ ጊዜ ዳኛው አጃቢዎቹን ይዞ ወደ ቤታቸው ሲመጣ ጎበዟ ሚስት በጣም ያረረ ዳቦ ጋግራ የዶሮ ላባ ያለበት ዶሮ ወጥዶሮ ወጥ ከእንጀራ ጋር በማባያነት የሚቀርብ ወፍራም ማጣቀሻ ነው፡፡ ሰርታ ጠበቀቻቸው፡፡ ዳቦውንም ወርቃማ ማቅረቢያ ላይ አድርጋ ዶሮ ወጡን ወርቃማ ክዳን ባለው ሳህን ስታቀርብ ዳኛው በጣም ተደሰተ፡፡
እናም “ይህች ሰው ጎበዝ ብቻ ሳትሆን ጥሩ ባለሙያም ናት፡፡” ብሎ ሰዎቹ ድስቱን ከፍተው እንዲበሉ ነገራቸው፡፡
ላባ ያለበትን ወጥና ያረረውን ዳቦ በተመለከቱ ጊዜ ግን ዳኛው “አይይ፣ይህች ሴት እንዳሰብናት ጎበዝ አይደለችምና እዚሁ ትቆይ፡፡” ብሎ ፈረደ ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|