የመነኩሴው ምርቃት
ተራኪው የማይታወቅ
አንድ ወንድ ልጅ የነበራቸው ባልና ሚስት ነበሩ፡፡ እነርሱም አንድ ቀን “እኛ እያረጀን ነውና ለልጃችን ሚስት ልንፈልግለት ይገባል፡፡” ብለው ለልጃቸው ሚስት አምጥተለውለት ልጁም በሃሳባቸው በመስማማት ሚስት አግብቶ አንድ ልጅ ወለደ፡፡ ከዚያ በኋላ ታዲያ በስራ ምክንያት መንደሩን ለቆ በመውጣትና ከተማ ውስጥ ካሉት ቤቶች ወደ አንዱ በመሄድ ስራ ቢጠይቅም ሰዎቹ እነርሱ ዘንድ ስራ እንደሌለ ነግረውት ወደ ሌላ ቤት አመላከቱት፡፡ ሁለተኛው ቤት ግን መነኮሳት የሞሉበት ነበር፡፡ እነርሱም “ከእኛ ጋር ምን ያህል ትቆያለህ?” ብለው ሲጠይቁት “አራት ወይም አምስት ወር ብቻ ነው የምቆየው፡፡ የምጦረው አባት አለኝና፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡
ሆኖም መነኩሴዎቹ “እኛ የምንፈልገው አብሮን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰው ነው፡፡” ሲሉት በሃሳቡ ተስማማ፡፡
ሌላኛውም መነኩሴ ልጁን ተምሮ እንደሆነ ሲጠይቀው “አዎ! የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡” ብሎ መለሰ፡፡
እነርሱም ብዙ ኃላፊነቶችን በመስጠት ወንበር ላይ ተቀምጦ የመነኩሴዎቹን ገቢ እንዲሰበስብ ቀጠሩት፡፡
ልጁም ከመነኩሴዎቹ ዘንድ ለአስር አመታት ከሰራ በኋላ “አሁን ወደ ቤተሰቤ መሄድ አለብኝ፡፡” ሲላቸው እነርሱም በጥያቄው ተስማምተው 400 ብርብር የኢትዮጵያ ህጋዊ የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ሰጡት፡፡
እርሱም “ሌሎቹ ሰራተኞቻችሁ በሄዱ ጊዜ ትመርቋችኋላችሁ፡፡ ለምንድነው እኔን የማትመርቁኝ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡
እነርሱም “ሌሎቹንማ ለእያንዳንዱ ምርቃት ኀኸኸኀደከደከከደከደከደከ ሀህለከደመበቨመቸቨመከ፤ልድፍል፤ድል፤ደ፤ለ፤ዶፈ100 ብር አስከፍለናቸዋል፡፡” አሉት፡፡
ልጁ ታዲያ “ምርቃታችሁንም ገንዘቡንም ስጡኝ፡፡” ሲላቸው ሶስት ጊዜ መርቀውት 300 ብር ከከፈለ በኋላ የቀረው ገንዘብ 100 ብር ብቻ ነበር፡፡
ምርቃቶቹም፤ በምታውቀው መንገድ ብቻ ተጓዝ፣ ማንም ሰው በመንገድህ ላይ የጠየቀህን አድርግ፣ በምታየውም ሆነ በምትሰማው ነገር አትበሳጭ የሚሉ ነበሩ፡፡
ልጁም 100 ብሩን ይዞ መነኩሴዎቹ (የታሸገ) ደብዳቤ ከሰጡት በኋላ ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ እንዲከፍተው ነግረውት ሄደ፡፡
በመንገዱም ላይ ሁለት ምስኪን ሰዎችን አግኝቶ እየተጨዋወቱ አብረው መጓዝ ጀመሩ፡፡ በመንገዳቸውም ላይ ከአንድ መስቀለኛ መንገድ አጠገብ ደረሱ፡፡
ልጁም “ከእናንተ ጋር ነው መሄድ ያለብኝ፡፡” ሲላቸው አንደኛው ሰው “ያንን መንገድ አታውቀውምና ወደዚያ አትሂድ፡፡” አለው፡፡
ይህንንም ብለው ሁለቱ ሰዎች ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲሄዱ ልጁ በሚያውቀው መንገድ ተጉዞ ከአንድ ወንዝ አጠገብ ሲደርስ ከፍተኛ ጩኸት ሰማ፡፡ በዚህ ጊዜ ወደ አንድ ጉብታ ሮጦ ሲመለከት ሁለቱ ሰዎች በሽፍቶች ሲደበደቡ አየ፡፡
ይህንንም ባየ ጊዜ ለራሱ “መነኩሴዎቹ ባይመርቁኝ ኖሮ እንደነዚያ ሰዎች እደበደብ ነበር፡፡” አለ፡፡
ወደ ሌላኛው አቅጣጫም ባየ ጊዜ አንድ ከፍተኛ ብርሃን ስለተመለከተ የብርሃኑን አቅጣጫ ተከትሎ ሄደ፡፡ ብርሃኑ የታየው ከአንድ ቤት ሲወጣ ነበርና ቤቱ ጋ ደርሶ ሲያንኳኳ አንድ የተከበሩ አዛውንት በሩን ከፍተው አስገቡት፡፡ አዛውንቱም ሰው ውሃ አምጥተው እጅና እግሮቹንበኢትዮጵያ ባህል የክብር እንግዳ እግር ማጠብ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን እድሜን ከማክበር የተነሳ ታላቅ ታናሽን አያጥብም፡፡ ሊያጥቡ ሲሉ እርሳቸው በእድሜ ከእርሱ የሚበልጡ ስለነበሩና የተከበሩ ስለነበሩ ሃፍረት ይዞት እምቢ አለ፡፡
ሆኖም በመጨረሻ መነኩሴዎቹ የነገሩትን አስታወሰ - ማንም ሰው በመንገድህ ላይ የጠየቀህን አድርግ፡፡ ስለዚህ አዛውንቱ ሰው እግሮቹን አጥበው ምግብ ከሰጡት በኋላ ምግቡን በላ፡፡ ከዚያም አዛውንቱ ሰው አይነ ስውር ሴት ልጅ አመጡለት፡፡ እርሱ ከሚመገብበትም ላይ እንዲያጎርሳት ነገሩት፡፡ ልጁም የልጅቷን ማንነት ማወቅ ቢፈልግም በሁለተኛው ምርቃት ምክንያት ምንም ነገር አልተናገረም፡፡ በመንገድህ ላይ የምታገኘውን ነገር ሁሉ ተቀበል፡፡ ስለዚህ ምግቡን ሰጣት፡፡ ከዚያም አዛውንቱ ሰው ልጁን ከመቃብር በላይ ካለው አልጋ ላይ እንዲተኛ ሲነግሩት ትዕዛዛቸውን ፈፀመ፡፡
በማግስቱም በጠዋት ከእንቅልፉ ተነስቶ “አሁን ወደቤቴ መሄድ አለብኝ፡፡” አለ፡፡
አዛውንቱም “መልካም፣ ያደረከው ነገር ሁሉ በጣም ድንቅ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ተቀብለሃል፡፡ ሴትየዋ አይነ ስውር የሆነችው በእኔ ምክንያት ነው፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜ እንዳገባት ትነዘንዘኛለች፡፡ መቃብሩም ትዕዛዜን ያልፈፀሙ ሰዎች የሞሉበት ነው፡፡ አንተ ግን ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ ፈፅመሃል፡፡” ብለውት 10000 ብር ሰጡት፡፡ ከዚያም መንገዱን ቀጥሎ እየተጓዘ ሳለ ከአንድ ቤተክርስቲያን ዘንድ ሲደርስ ሁለት ሰዎች ራቁታቸውን ሲፀልዩ አያቸው፡፡
እርሱም “ምን እያደረጉ ነው?” ብሎ ጠየቀ፡፡
በድርጊታቸውም ተናደደ፡፡ መሬት ላይ ሲንከባለሉም አያቸው፡፡ ሆኖም ሶስተኛውን ምርቃት አስታወሰ፡፡ በመንገድህ ላይ በምታየውም ሆነ በምትሰማው ነገር አትበሳጭ፡፡
እናም ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከዚያም ብዙ ሰዎች ሲሯሯጡ አይቶ ስለተረበሸ “እነዚህ ሰዎች ምንድናቸው?” ብሎ ጠየቀ፡፡
እነርሱም “ከአስር አመታት በፊት ልጅ የጠፋበት ሰው የሚረዳው ዘመድ ስለሌለው ገንዘብ እየሰጡት ነው፡፡” ብለው ነገሩት፡፡
እርሱም “ልጁ እኔ ነኝ፡፡” አለ፡፡
እነርሱም “አባትህና ልጅህ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ እየፀዩ ነው፡፡ ራቁታቸውን ሲንከባለሉ ያየሃቸው እነርሱ ናቸው፡፡” አሉት፡፡
በዚህ ጊዜ ወደ ኋላው ተመለሰ፡፡ ነገር ግን እዚያ በደረሰ ጊዜ የመነኩሴዎቹን ደብዳቤ አስታውሶ ሲከፍተው 400 ብር አገኘ፡፡ ከዚያ በኋላ በደስታ አብረው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|