ክፉ አመሎች
ተራኪው የማይታወቅ
በአንድ ወቅት ወንዶች ሁሉ ሊያገቧት የሚመኟት ቆንጆ የአፋር ልጃገረድ ነበረች፡፡ ከወንዶቹም አንዱ አግብቷት ሲያደበቃ ብዙም ሳይቆይ ይፈታታል፡፡ ሁለተኛውም K=ያገባት የፈለገ ሰው ይህንኑ K=ጠይቃት ሄዶ ከአንድ ዛፍ ስር ተቀምጠው ይጫወቱ ጀመር፡፡
“ለምን ከመጀመሪያ ባልሽ ተፋታሽ?” ብሎ ሲጠይቃት “እኔ አላውቅም ባለቤቴ ሶስት የሚያስጠሉ ነገሮች ስላሉበሽ ባለቤቴ መሆን አትችይም፡፡ አለኝ፡፡” ብላ መለሰችለት፡፡
እናም ሁለተኛው አድናቂዋ በጥንቃቄ ሲመለከታት አቀማመጧ ቅጥ ያጣ በመሆኑ Hõ[} ገላዋን ውስጥ ድረስ አየው፡፡ ይህ ለአፋር ሴት ጥሩ አይደለም፡፡
ከዚያም እንዲህ አላት “እኔም ከሶስቱ አንዱን አስቀያሚ ነገር አውቄዋለው፡፡”
እሷም ቀና ብላ ተመልክታው “ምን ማለትህ ነው? አንተ የውሻ ልጅ” ብላ የብልግና ቃል ጨምራ ሰደበችው፡፡
እሱም “አሃ! አሁን ደግሞ ሁለተኛውን አስቀያሚ ነገር ስላወቅሁት ሶስተኛውን ለማወቅ መጠበቅ ያለብኝ አይመስለኝምና ተነስቼ ልሂድ” ብሎ ወሰነ፡፡
በዚህም አኳኋን የተቀመጠችበት ዛፍ ሥር ትቷት ሄደ፡፡
ይህ ተረት መልክ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|