አህያና ጅብ
በአሎ ያዮ ቡራሌ የተተረከ
ከረጅም ግዜ በፊት ጅብ በሰማይ ላይ አህያ ደግሞ በምድር ላይ ይኖሩ እንደነበር ያውቃሉ፡፡
እናም አያ ጅቦ የራሱን ድምፅ ስለሚወደው እያጓራ ይዞር ነበር፡፡ አህያም ብዙ ትጸልይና እንዲህ ትል ነበር፡፡ እባክህ ይህንን ድምጹ ያማረ ወደ ምድር አውርደው፡፡ ጅብም ወደ ምድር ወረደ፡፡ ጅብም አህያን ባየ ግዜ ረጃጅም ጆሮዎቹ ቀንድ ስለመሰሉት እ”ÇèҨ< በመፍራቱ ሊበላውም ቢፈልግ ፈርቶ ተወው፤ አህያው ደግሞ ከዚህ የውብ ድምጽ ባለቤት ጋር ጓደኝነት ለመመስረት በጣም ፈለገ፡፡
እናም ጅቡ ሊበላው ሲፈልግ አህያው ደግሞ ጓደኛ ሊያደርገው ይፈልግ ነበር፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ጅቡ አህያውን እንዲህ አለው፡፡ “ለምን ተገናኝተን እግር ኳስ አንጫወትም?”
አህያውም “ይሄማ ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡” አለው፡፡
እናም ኳስ ሜዳ ላይ ተገናኙ፡፡ ጅቡም አህያውን “ተመልከት! ስለታማ መሳሪያዎችን ይዘን መጫወት አይፈቀድልንም፡፡ ስለዚህ መሳሪያዎችህን አስቀምጠህ ናና እንጫወት፡፡” አለው፡፡ አህያውም “የምን መሳሪያ ነው የምትለው”? ብሎ ጠየቀው፡፡ ጅቡም “እነዚያ ጭንቅላትህ ላይ ያሉትን ቀንዶች ማለቴ ነው” አለው፡፡ አህያውም “እነዚህ ቀንዶች አይደሉም፡፡ እንዴት ለስላሳ እንደሆኑ ተመልከት፡፡ ጆሮዎቼ ናቸው፡፡” አለው፡፡
ጅቡም ሁለቱን ጆሮዎቹንና ጭራውን ገንጥሎ ጣላቸው፡፡
አህያውም “ምን እያደረክ ነው? ያደረከው ነገር የሚያወዳጅ አይደለም፡፡” ብሎ ጮኸ፡፡
ጅቡም “ጓደኛሞች እንሆናለን ብለህ አስበህ ከሆነ በጣም ደደብ ነህ፡፡” አለው፡፡
በሚቀጥለው ቀን አህያውና ጅቡ ከወንዝ ውሃ እየጠጡ ነበር፡፡ አህያ በወንዙ በታችኛው ክፍል ሲጠጣ ጅቡ በላይኛው ክፍል ይጠጣ ነበር፡፡
ጅቡም ወደ አህያው ዞር ብሎ “አንተ ቆሻሻ! ውሃዬን እያቆሸሽክ ነው፡፡” አለው፡፡
አህያውም “ይህ በፍጹም ሊሆን አይችልም፡፡ በታች በኩል እየጣጠሁ ያለሁት” አለው፡፡
ጅቡም “እያቆሸሽክብኝ ነው እኮ የምልህ፡፡” አለው፡፡ አህያውም “እኔን ልታጠቃኝ ከፈለክ ምክንያት አትለቃቅም::” አለው ይባላል፡፡
የተረቱም መልዕክት ጠላትህ ደካማ ጎንህን እንዲያውቅ ካደረግህ ያጠቃሃል ማለት ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|