መነሻ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የአሣ ማጥመድ ታሪክ
የአሣ ማጥመድ ታሪክ
በኤጋሲ ረታ የተተረከ
በድሮ ጊዜ ሰዎች ከወንዝ ዳር በመሰባሰብ የብርብራ ዛፎችን ፍሬዎች በማሰገሪያነት ተጠቅመው አሣ ያጠምዱ ነበር፡፡
ታዲያ ይህንን ሲያደርጉ ውሃው እየሞላ፣ እየሞላ፣ እየሞላ ይሄድ ነበር፡፡
ታዲያ ውሃው ሞልቶ ሲያበቃ ለሁለት ስለተከፈለ ሰዎቹ በወንዙ ተወስደው ሄዱ፡፡
ግማሾቹ ሰዎች ወደ ዝሆንነት ግማሾቹ ደግሞ ወደ አዞነት ሲለወጡ ሌሎች ጭራ አብቅለው ነበር፡፡
ወደ ዝሆንነት ወደ አዞነትና ወደ ጦጣነት ከተቀየሩ በኋላ ቤታቸውን ከውሃ በታች በባህር ውስጥ ሰርተው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|