ኤሊና ጥንቸል
በኪዊ ጃሬድ የተተረከ
አንድ ኤሊና አንድ ጥንቸል ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ሁለቱም ወንዶች ነበሩ፡፡ አብሮ ከመኖር የተነሳ በጣም ስለተላመዱ ወሲብ እንፈፅም አሉ፡፡
ጥንቸሉም በሩጫው ፍጥነት በመተማመን በቅድሚያ “እኔ ላድርግ” አለ፡፡
ኤሊው ግን “ቀድሜ እኔ ላድርግ::” ብሎ ሞገተው፡፡
በመቀጠልም ኤሊው “እኔ በጣም ቀርፋፋና ጀርባዬ ላይ ሽፋን ቢኖረኝም በዚህ ላሸንፈው እችላለሁ፡፡” ብሎ አሰበ፡፡ ከዚያም ኤሊው “የመራቢያ አካሌ በጣም ጠንካራ ስለሆነ አታሸንፈኝም ስለዚህ እኔ መጀመሪያ ላድርግ” አለው፡፡
ሆኖም ጥንቸሉ መጀመሪያ እንዲያደርግ ተስማሙ
“በቀላሉ ለማድረግ እንድንችል ውሃ ከወንዙ ቀድቼ ልምጣና እኔ መጀመሪያ አደርጋለሁ፡፡”
ኤሊውም “እሺ” አለ፡፡
አቦቦ የተባለውም ጥንቸል ውሃውን በአፉ ሞልቶ ሲመለስ ኤሊው ሌላ ቦታ ተደብቆ “ውሃውን አምጣልኝ ውሃውን አምጣልኝ” አለው፡፡
“የት ነው ያለኸው አያ ኤሊ?”
ኤሊውም “የት ነህ የት ነህ ላገኝህ እኮ አልቻልኩም” አለው፡፡ ጥንቸሉ ቢመጣ ኤሊው ተሰወረ፡፡
ጥንቸሉም “ቀጠሮ ነበረን አንተ ግን እዚህ የለህም፡፡” አለው፡፡ ኤሊውም “የመረጥነው ቦታ ጥሩ ስላልሆነ ወደ ወንዙ ተመልሰህ ውሃ ቀድተህ ና::” አለው፡፡
እንደተነገረውም ጥንቸሉ ለሁለተኛ ጊዜ ውሃ ሊቀዳ ሲሄድ አሁን ኤሊው ተደበቀ፡፡ ጥንቸሉም በዚህ በጣም በመናደድ ይህ ቀርፋፋ እንስሳ ደጋግሞ ወደ ወንዝ ከሚልከው ሽፋኑን ቢሰብረው እንደሚሻል አሰበ፡፡
የዚህ ተረት መልዕክትም ሌሎች ከእናንተ እንደሚያንሱ በመቁጠር አትናቋቸው የሚል ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|