ሴቷና አንበሣው
በፋጡማ አሊ የተተረከ
አንድ ባሏ የሚበድላት ሴት ነበረች፡፡ ሁልጊዜም ይደበድባት ነበር፡፡ የሚፈልገውን ሁሉ ብታደርግለትም እንጀራናእንጀራ ብዙውን ጊዜ ከጤፍ የሚሰራ ከብና ጠፍጣፋ ምግብ ነው፡፡ ወጥወጥ ከእንጀራ ጋር የሚቀርብ ማባያ ነው፡፡ ብታቀርብለትም ሁልጊዜ ስለሚደበድባት በጣም ትቸገር ነበር፡፡
“ሁልጊዜ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ እርሱ ግን ሁልጊዜ ይደበድነኛል፡፡ ምን ባደርግ ይሻለኝ ይሆን?” ብላ ታማርር ነበር፡፡
በየጊዜው ከጎረቤቶቿ፣ ከዘመዶቿ፣ ወዘተ ምክርን ብትጠይቅም በጣም ትረበሽ ነበር፡፡
እነርሱም እዚህ ሂጂ፣ እዚያ ሂጂ፣ መፍትሔ ታገኛለሽ እዚያ መድኃኒት አለ፣ እዚህ መድኃኒት አለ፡፡ እያሉ ይነግሯት ነበር፡፡
አንድ ብልህ ሰው ዘንድም ሄደች
እርሱም “ችግርሽ ምንድነው?” ብሎ ጠየቃት፡፡
እሷም እንዲህ አለችው “የሚፈልገውን ሁሉ ባደርግለትም የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ብሰጠውም ባሌ ሁልጊዜ ይደበድበኛል፡፡ ለዚህ ምንም መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም፡፡”
እሱም “እዚህ ምንም መፍትሔ የለም፡፡ ምንም አይነት መድኃኒት ልሰጥሽ አልችልም፡፡ ከቻልሽ ግን የአንበሣ ቅንድቦች ብታመጪልኝ አንድ ነገር አደርግልሻለሁ፡፡” አላት፡፡
ይህንን ስትሰማ መጀመሪያ በጣም ፈራች፡፡
“የአንበሣ ቅንድቦች እንዴት ላገኝ እችላለሁ?” ብላ አሰበች፡፡ ከዚያም አንዲት ፍየል ከገደለች በኋላ በዚህ ዓይነት የአንበሣ ቅንድብ ማግኘት እችል ይሆናል፡፡ ብላ አሰበች፡፡
አንበሣ ሊያገኛት ከማይችልበት ዛፍ ላይ ወጥታ ተቀመጠች፡፡ በመጀመሪያውም ቀን ፍየሏን ገድላ ትልቅ ሥጋ ለአንበሣው ወረወረችለት፡፡ ይህንንም በተከታታይ በሰባት ቀናት አደረገች፡፡ አንበሳውም በተደጋጋሚ የሚወረወርለትን ሥጋ እየበላና ከዛፉ ስር ያለውን ውሃ እየጠጣ ቆየ፡፡ በሰባተኛውም ቀን አንበሣው ከእንቅልፉ ይነቃ እንደሆነ ለማየት አንዲት ቁራጭ እንጨት ብትወረውርበትም አንበሳው አልነቃም፡፡
“እንግዲህ ቅንድቦቹን የማገኝበት ጊዜው አሁን ነው፡፡” ብላ ከዛፉ በመውረድ ቅንድቦቹን ወስዳ ሄደች፡፡ ወደ ብልሁ ሰው ዘንድም አመራች፡፡
“እንዴት ልታመጪ ቻልሽ?” ብሎም ጠየቃት፡፡
“ለሰባት ቀናት ያህል የፍየል ሥጋ ስወረውርለት ቆይቼ በመጨረሻም ቀን እንቅልፍ ሲጥለው ቅንድቦቹን ወሰድኩ፡፡” አለችው፡፡
ብልሁም ሰው “ታዲያ ባልሽንም የምታሸንፊው ልክ እንደዚህ ነው፡፡ ሌላ መፍትሔ የለውም፡፡ እሱ እንደሚፈልገው በመሆን በዘዴ ያዢው፡፡” አላት ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|