መነሻ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሃብታምና ደሃ ወንድማማቾች
ሃብታምና ደሃ ወንድማማቾች
በፋጢማ አሊ የተተረከ
አንደኛው ሃብታም ሌላውን ድሃ የሆኑ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ ሃብታሙ ወንድም ድሃ ሰዎችን በፍፁም አይወድም ነበር፡፡
ድሃው ወንድም ግን ድሃ ቢሆንም ጥሩ ሰው ነበር፡፡ ድሃው ወንድም ለእንግዶች የሚያካፍለው ነገር ባይኖረውም ያለውን ይሰጥ ነበር፡፡ ሃብታሙ ወንድም ግን ማንም ሰው ወደ እርሱ ቤት እንዲመጣ አይፈልግም ነበር፡፡
እንግዶች ወደ ድሃው ወንድም በመጡ ጊዜ ድሃው ወንድም “እዚህ ልናካፍላችሁ የምንችለው ምንም ማረፊያ ቦታ ስለሌለን ልናሳድራችሁ አንችልምና እባካችሁ ወንድሜ ዘንድ ሄዳችሁ ጠይቁት::” ይላቸዋል፡፡
እነእርሱም ወደ ሃብታሙ ወንድም ቢሄዱም እንደተለመደው “አዚህ ለእናንተ የሚሆን ቦታ የለም፡፡” ብሎ አባረራቸው፡፡
ተመልሰውም ወደ ድሃው ወንድም ቤት ሄዱ፡፡
ከሃብታሙ ወንድም ቤት ተባረው የተመለሱ እንግዶችም ድሃው ሰው “አንተ አትቸገር ከደጃፍህ ላይ አድረን ጠዋት እንሄዳለን::” አሉት፡፡
ድሃው ወንድምና ሚስቱም “የምትመገቡትን ምን ልንሰጣችሁ እንችላለን?” ብለው ጠየቋቸው፡፡
“አትቸገሩ የራሳችንን ምግብ ይዘናል፡፡” ብለው መለሱላቸው፡፡ የሚጠጡትንም ውሃ ሰጣቸው፡፡ ውሃውንም ከጠጡና የራሳቸውን ምግብ ከበሉ በኋላ በዚያኑ ሌሊት ተነስተው ሄዱ፡፡
ባልና ሚስቱም ከእንቅልፋቸው ሲነቁ እንግዶች ሄደው ቤታቸው ግን በሃብት ተሞልቶ አገኙት፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|