ድመት እንዴት የሴት ጓደኛ እንደሆነች
በአብዱልሃኪም አብዱላሂ ጅብሪል የተተረከ
በዓለም መጀመሪያ ወቅት ድመት የጫካዋ ሚዳቋ ጓደኛ ነበረች፡፡ ሆኖም በአንድ ወቅት አንበሳ ወደ ጫካው መጥቶ ሚዳቋዋን በመተናኮል ሲገድላት ድመቷ አንበሳ የተሻለ እንደሆነ ስላሰበች የአንበሳ ጓደኛ ሆነች፡፡ ነገር ግን አንድ የዝሆን መንጋ መጥቶ አንበሳውን ታግሎ ሲገድለው ስታይ የዝሆኖች ጓደኛ ሆነች፡፡ ከዚያም ሰው ዝሆንን ሲገድል ድመቷ “አሃ! ይህ ከዝሆን የተሸለ ፍጡር ነው፡፡” በማለት የሰው ጓደኛ ሆነች፡፡ ሰውየውም ወደቤቱ እንደተመለሰ ከሚስቱ ጋር መጣላት ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ሚስቱ ዱላ ይዛ ወደ ባሏ እየሮጠች “የት ነበርክ?” ብላ ጮኸችበት፡፡ አከታትላም ብዙ መጥፎ ቃላት እተናገረች ስለጮኸችበት ሰውየው ሮጦ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ድመቷ “አሃ! ሴትየዋ ከሰውየው የተሻለች ነች፡፡” በማለት የሴትየዋ ጓደኛ ሆነች ይባላል፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|