ውሻ፣ ፍየልና አህያ
በአብዱል አሚን አህመድ የተተረከ
በአንድ ወቅት ውሻ፣ ፍየልና አህያ ወደ ሌላ አገር አብረው ለመሰደድ ይነሳሉ፡፡ አውቶብስ ላይም ተሳፈሩ፡፡ ውሻው አስር ብር ሲኖረው አህያዋ አምስት ብር ነበራት፡፡ ፍየሏ ግን ምንም ገንዘብ አልነበራትም፡፡
የአውቶብሱ ቲኬት ዋጋ አምስት ብር ስለነበረ ውሻው ለቲኬት ቆራጯ አስር ብር ሲሰጣት መልስ አልሰጠችውም፡፡ ፍየሏ ምንም ገንዘብ ስላልነበራት አውቶብሱ ውስጥ ተደብቃ ገባች፡፡ አህያውም የራሱን ሂሳብ አምስት ብር ከፍሎ አውቶብሱ የመጨረሻው ፌርማታ ሲደርስ ሁሉም ወረዱ፡፡
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ውሻ ሀልጊዜ አውቶብስ እየተከተለ “አምስት ብሬን አምጣ! አምስት ብሬን!” እያለ ሲሮጥ ፍየል ግን “ቲኬት ቆራጯ ገንዘብ አምጪ ትለኛለች፡፡” በማለት ከአውቶብሱ ትሸሻለች፡፡ አህያዋ ታዲያ የራሷን አምስት ብር ስለከፈለች ሁልጊዜ በመረጋጋትና በደስታ ስሜት ከአውቶብስ አትሸሽም፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|