ቀበሮውና ሚዛኑ
በዩሱፍ አድም ማንደሬ የተተረከ
ከብዙ ዓመታት በፊት ሁለት ጦጣዎች አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ምግብ ፍለጋ ወጥተው የሚበሉት ነገር አገኙ፡፡
ሆኖም በምግቡ ላይ መጣላት ጀመሩ፡፡
ስለዚህ “ወደ ቀበሮው ዘንድ ሄደን እርሱ ይገላግለን፡፡” ብለው ወደ ቀበሮው ሄዱ፡፡ ቀበሮውም ጉዳዩን በጥሞና ካዳመጠ በኋላ “ምግቡን ሁለት እኩል ቦታ ማካፈል ስላለብኝ ሚዛን መጠቀም አለብኝ፡፡ ነገር ግን አሁን ሚዛን በእጄ የለም፡፡ ዛሬ ጠዋት ሚዛኑን ለአንበሳው ስላዋስኩት ወደ አንበሳው ሄደን ምግቡን እናካፍለው፡፡” አለ፡፡
እንደደረሱም ቀበሮው አንበሳውን ተጣርቶ ጉዳዩን ነገረው፡፡ እንዲህም አለው “አንበሳ ሆይ! እነዚህን ጦጣዎች አስታርቃቸው፡፡” ይህንንም ብሎ ቀበሮው ወደ አንበሳው ዋሻ ሳይገባ ተመልሶ ሄደ፡፡ ጦጣዎቹም የተውትን ምግብ አንስቶ ራሱ በላው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ሁለቱ ጦጣዎች ችግራቸውን ለአንበሳው መንገር ጀመሩ፡፡ ነገር ግን አንበሳው እነርሱን መብላት አንጂ መዳኘት አልፈለገም ነበርና በላቸው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|