የዝንጀሮ አለቃ
በቦንሳሞ ሚኤሶ የተተረከ
በአንድ ወቅት ብዙ የዝንጀሮ መንጋ የሚከተለው ግዙፍ ዝንጀሮ ነበረ፡፡ እሱም እውነተኛ ጨቋኝ ስለነበረ ሁሉንም ያሰቃያቸው ነበር፡፡
ነገር ግን ሌሎች ብዙ ግዙፍ ዝንጀሮዎች መንጋው ውስጥ ስለነበሩ ሌሎቹ ተራ ዝንጀሮዎች ትዕዛዝ የሚሰጠው ዝንጀሮ የትኛው እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አልቻሉም፡፡
ስለዚህ አለቃቸውን “ምንነትህን በትክክል የምንለይበት ለየት ያለ ምልክት ቢኖርህ ያንተን ትዕዛዝ በቀላሉ መከተል እንችላለን፡፡” አሉት፡፡
እሱም “እንግዲያው ይሁን፡፡ እኔም ጭንቅላቴ ላይ ጥምጥም ስለማስር ይህንን ሳደርግ እናንተ ደግሞ እያንዳንዷን የትዕዛዜን ቃል መፈፀም አለባችሁ፡፡” አላቸው፡፡
እናም አንድ ትልቅ ዝንጀሮ አለቃው ጭንቅላት ላይ ጥምጥም ካሰረለት በኋላ አለቃው “እንግዲህ ተስማምተናል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የምነግራችሁን ነገር ሁሉ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ምንም አይነት እምቢተኝነት አልፈልግም፡፡” አላቸው፡፡
በዚህም መሰረት አለቃው ሲዘል ሌሎቹም አብረው ይዘላሉ፡፡
እርሱ ሲቀመጥ እነርሱም ይቀመጣሉ፡፡ እርሱ ሲጮህ ሌሎቹም ተከትለውት ይጮሃሉ፡፡
ጊዜ እየገፋ ሲሄድ የራስ ጥምጥሙ እየጠበቀ ስለሄደ አለቃው ከተቀመጠ በኋላ “አምላኬ ሆይ፣ ይህ ጥምጥም እየጎዳኝ ነው፡፡” ብሎ ጥምጥሙን አውልቆ በእጁ ያዘው፡፡
ሌሎቹም ዝንጀሮዎች ሁሉ ተቀምጠው “አምላኬ ሆይ፣ ይህ ጥምጥም እየጎዳኝ ነው፡፡” አሉ፡፡
እነርሱም “ይህ ነገር ሊገድለኝ ነው፡፡” አሉ፡፡
ከዚያም አለቃው ከተቀመጠበት አለት ላይ ሲወድቅ ሁሉም እሱን በመከተል ከአለቱ ላይ ወደቁ፡፡ ከዚያም እርሱ መታገል ሲጀምር እነርሱም መታገል ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም እርሱ ሲሞት እነርሱ ዳኑ፡፡
የዚህ ታሪክ መልዕክትም የማይቃወሙና ሁልጊዜ እሺ የሚሉ ተከታዮች ካሉህ ችግር ላይ መሆንህን እወቅ የሚል ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|