ተጓዡ
በዶዮ ሁካ የተተረከ
በአንድ ወቅት በጣም፣ በጣም ረጅም መንገድ የተጓዘ መንገደኛ ነበር፡፡ ለብዙ ቀናት ከተጓዘ በኋላ ውሃ በጣም ጠማው፡፡
እናም ከአንዲት ጎጆ አጠገብ ሲደርስ ቆም ብሎ ጎጆዋ ውስጥ ያለችውን ሴት ሰላምታ እንኳን ሳይሰጣት “ውሃው እንዴት ነው? ውሃ አለሽ? “ ብሎ ጠየቃት፡፡
አሮጊቷም ሴት “እንደምንድነህ?ደህና ነህ? ሰላምታ እንኳን ሳትሰጠኝ ውሃ መጠየቅህ በጣም ቢጠማህ ነው፡፡” ብላ መለሰችለት፡፡
መንገደኛውም “እንግዲያው ይህንን ካልሽና ምን ያህል እንደተጠማሁ ካወቅሽ በጣም አስተዋይ ሰው ነሽ ማለት ነው፡፡” አላት፡፡
እርሷም “አዎ ነኝ፤ ነገር ግን ውሃውን ልሰጥህ አልችልም ምክንያቱም ባለቤቴ አህዮችን የሚያኮላሽ ሰው ስለሆነ ብዙ ውሃ ያስፈልገዋል፡፡ እጆቹን በየቀኑ ባይታጠባቸውም እንኳን ሲሞት የሚታጠብበት ውሃ እያጠራቀምን ነው፡፡” አለችው፡፡
ተጓዡም ሰው እንዲህ አለ “ለተጠማ ተጓዥ ጠብታ ውሃ መከልከልሽ ክፉ ሰው ያሰኝሻል፡፡”
እርሷም “አንተ የጋምቤላ ሰው ሆይ፣ ማንም ብሎኝ የማያውቀውን እንዴት ክፉ ብለህ ደፍረህ ትናገረኛለህ? ልጆች ሁሉ፣ ከብቶችና ፍየሎች እንኳን ክፉ ብለውኝ አያውቁም፡፡” አለችው፡፡
መንገደኛውም “ምናልባት ፍየሎቹ በሰላም እየኖሩ ይሆናል፡፡ እኔ ግን አንቺም ሆንሽ አነጋገርሽ ክፉ መሆናችሁን ነው የማውቀው፡፡” አላት፡፡
ሴትየዋም “ስለ ክፋት ካነሳህ ተግባቢ ሰዎች ብቻ ናቸው እርስ በርሳቸው የሚሞጋገሱት፡፡ ክፉ የሆኑ እንግዳ ሰዎች ግን ከጎጆው ደጃፍ ላይ ይቆማሉ፡፡ ለምን አትገባም?” ብላ ወደ ውስጥ ጋበዘችው፡፡
እርሱም “ያንቺ እዚህ መኖር ለእኔ ትርጉም አለው፡፡ ሁሉም ሰው የተለያየ ነገሮችን ማሞጋገስ ይወዳል፡፡ እኔ ደግሞ ገብቼ አንቺን ላወድስሽ እፈልጋለሁ፡፡” ብሏት ወደ ጎጆው በመግባት አብረው በደስታ መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|