የፀማይ ጎሳ አመጣጥ
በኦይታ ኦሮ የተተረከ
በፀማይ ዘጠኝ ጎሳዎች አሉ፡፡ ታዲያ በአንድ ወቅት ያልተገባውን አድርገው እናት ከወንድ ልጇ ጋር፣ አባትም ከሴት ልጁ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ይፈፅሙ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ሞት አልነበረም፡፡ እናም አምላክ ተቆጥቶ “ያልተገባውን በማድረግ ሃጢአት ስለፈፀማችሁ ቅጣት ይገባችኋል፡፡” ብሎ ብዙ አይነት በሽታዎችን እንደ የሳምባ በሽታን የመሳሰሉትን ስለለቀቀባቸው ሰዎች መሞት ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም አምላክ በፀማይ ብሔረሰብ ውስጥ ላሉት ዘጠኝ ጎሳዎች ዘጠኝ ልጃገረዶችን ሰጥቷቸው ከዚያ በኋላ ከመጥፎ ድርጊታቸው ታቅበው በሰላም አብረው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|