ሞኙ ልጅ
በአይካበዳኔ ባሻ የተተረከ
አንድ በሩቅ አገር የሚኖር ዘላን ልጅ ከአህዮች ጋር የግበረ ስጋ ግንኙነት ይፈፅም ነበር፡፡ ከብዙ አመታት በኋላም ወደ ቤቱ ሲመለስ እናቱ ተራራ ስትወጣ የእናቱን ሃፍረተ ስጋ አየ፡፡
በዚህ ጊዜ “ያ ቁስል ምንድነው?” ብሎ ጠየቃት፡፡
እርሷም “ይህ ቁስል አይደለም፡፡ በኋላ ስታገባ ታውቀዋለህ፡፡” ብላ መለሰችለት፡፡
በኋላም አንዲት ልጅ አግብቶ “ቁስልሽ የታለ?” ብሎ ሲጠይቃት እግሮቿን አሳየችው “ተመልከት! ምንም ቁስል የለብኝም፡፡” አለችው፡፡
የዚያን እለት ምሽትም ፆታዊ ግንኙነት ባደረጉ ጊዜ አካሏ ቁስል ሳይሆን በአለም ላይ ካሉ ነገሮች ሁሉ የጣፈጠ እንደሆነ ተገነዘበ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ቦረና የተባለው ጎሳ አባላት መንደሩን በመውረር ብዙ ሰዎችን በጦር መግደል ጀመሩ፡፡
በዚህ ጊዜ የልጁ ሚስት “እንደ ሌላው ሰው እንሽሽ” ስትለው ያንን ቁስል መሳይ ነገር እየጠየቃት ከቤቱ የትም መሄድ እንደማይፈልግ ነገራት፡፡
ሆኖም እርሷ ከቤቱ ወጥታ ስትሄድ ተከትሏት ኋላ ኋላዋ ሲሄድ “ና እሰጥሃለሁ፡፡” እያለች ፊት ፊቱ ትሄድ ጀመር፡፡ እርሱም የፈለገውን እንደሚያገኝ እያሰበ ተከትሏት ሲሮጥ ከጦርነቱ አመለጡ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|